የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሜይዴይ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት በበጀት አመቱ በግልጽ ጨረታ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሜይዴይ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-ሜ001/2010ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሜይዴይ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት በበጀት አመቱ በግልጽ ጨረታ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃዎች ......... ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 3000.00 ብር
- የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ......... ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 4000.00 ብር
- የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች ................. ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 3000.00 ብር
- አላቂ የህክምና እቃዎች ......... ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 3000.00 ብር
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ......... ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 3000.00 ብር
- የተለያዩ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ......... ሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 8000.00 ብር
- የህትመት ስራዎች ......... ሎት 7 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 3000.00 ብር
- የተለያዩ ጥገና ስራዎች ......... ሎት 8 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 6000.00 ብር
- የመስተንግዶ ውሃና ቆሎ ......... ሎት 9 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 2000.00 ብር
- የደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ ......... ሎት 10 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 4000.00 ብር
- የካፌ አገልግሎት ......... ሎት 11 የጨረታ ማስከበሪያ (1 %) 3000.00 ብር
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን በ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው የግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ ከ3 ቀናት በፊት ናሙናውን በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው። በናሙና (ሳንፕል) ማቅረብ የማይቻሉ ቋሚ እቃ በፎቶ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም የት/ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ቦታው ድረስ በመሄድ እቃውን ያያል። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ አለባቸው። ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈፅመው ወኪል ከሆነ ከፍ/ቤት የተሰጠውን ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 350 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ሲመልሱ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተምና ፊርማ/ በአርሶ በኩል መሞላት ያለበት ተሞልቶ መመለስ አለበት።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና በምንሰጣቸው የዋጋ ቅፅ መሆን አለበት። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው ዋናውንና ኮፒውን የመወዳደሪያ ዶክሜንት በታሸገ በ4 /አራት/ ፖስታ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10ኛው የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባችዋል። ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ ብር 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ራሳቸው በሚያመርቱት ምርት መሆን አለበት ካደራጃቸው ወረዳ የጨረታ ማስከበሪያ ህጋዊ ደብዳቤ (CPO) እና የውል ማስከበሪያ 10% በተጨማሪም ያፀደቀላው አካል ህጋዊ ማንነት በመግለጽ መወዳደር እንዲችሉ እየገለፅን ሰነዱን በመውለድ እስክ 10 ኛው ቀን ድረስ የእቃዎችን ዝርዝር ዋጋ እና አይነት በመግለፅ የሰነድን ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ:- 011-2-31-01-18/011-2-13-74-56
አድራሻ፡- መርካቶ ጎጃም በረንዳ የድሮው ፋሲል ፋርማሲ ጎን (ከይርጋ ሀይሌ ህንፃ ከፍ ብሎ)
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሜይዴይ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት
