በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባሌ ዞን የደሎ መና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባሌ ዞን የደሎ መና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በ 2018 ዓ.ም የበጀት አመት፤ አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ህትመትና የህትመት ስራዎችን ፣ የደንብ ልብስና የልብስ ስፌት ስራ፣ የሞተር ላይክሎች ግዢና የጥገና ስራ፣ የሞተር ሳይክል ዕቃና ጎማ፣ የመኪና ጎማ ከነ ከለመዳሪው፣ የኮምፒውተር፣ የፎቶ ኮፒና የፕሪንተር ጥገና፣ የቴክኒክና ሙያ የተለያዩ የማሰልጠኛ መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለጨረታ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የሞተር ሳይክል፣ የደንብ ልብስ እና የኮምፒውተር ጥገና (TOT 2% ወይም 10%) (VAT 15%) ተመዝጋቢ የሆነ።
- ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈለና የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በሚቀርብበት ወቅት ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ በሰም በማሸግ መቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው ሰነድ በሚከፈትበት ወቅት ጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት የቁጥርም ሆነ የአኃዝ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከደሎ መና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የተገዛበት ደረሰኝ ጨረታው በሚከፈትበት እለት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታውን ማስከበሪያ /CPO/ አስር ሺህ ብር (10,000) ማስያዝ የሚችል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታ ለማስከፈት በሚቀርቡበት ወቅት ህጋዊ የውክልና ደብዳቤ ኦርጂናል እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውልና በ16 ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ጠዋት 3፡30 ሰዓት በማሸግ 4፡30 ሰዓት ላይ በደሎ መና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ያቀረቡ ተወዳዳሪዎች የጨረታው ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው።
- ደንብ ልብስ ላይ የምትወደዳሩ የምትወደዳሩበትን የልብስ ናሙና ይዛችሁ መቅረብ አለባችሁ፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ወይም ለኮምፒዩተር ጥገና የምትወደዳሩ የብቃት ማረገጋጫ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት ይኖረዋል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር:-0226680015/361/0915815858/0912821171/0923714383 መደወል ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባሌ ዞን የደሎ መና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
