Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ቱለፋ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ገነት ከተማ አለፍ ብሎ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0973 80 72 93
  • Website
  • Deadline13 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለጽሕፈት መሣሪያ 9000 ብር፣ ለቋሚ አላቂ 850 ብር፣ ለጽዳት እቃ 900 ብር እና ለመኪና ጎማ 7000 ብር
  • opening date2025-10-13 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Electronics Materials , Vehicle tire

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ/ ፅ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ለመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ/ ፅ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ለመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስለመግዛት ይፈልጋል፡-

ስለዚህ ተጫራቾች፡.

1 የጽህፈት መሣሪያ 2. ቋሚ አላቂ 3. የጽዳት እቃ 4 የመኪና ጎማ

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊክሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለጽሕፈት መሣሪያ 9000 ብር፣ ለቋሚ አላቂ 850 ብር፣ ለጽዳት እቃ 900 ብር እና ለመኪና ጎማ 7000 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.አ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈራረምና የድርጅቱን ክብ ማህተም በማድረግ ዋናና ኮፒውን በመለየት 2ቱንም ፖስታዎች ማለትም ዋናና ኮፒውን የተጫራቹን ስምና አድራሻ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ዕ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር6 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ ከ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቹ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች መ/ቤቱ ባዘጋጀው ናሙና መሰረት እቃዎቹን በማየት ዋጋውን ሞልቶ ማቅረብ መቻል አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን እንዳዋጭነቱ በተናጠል ወይም በጥቅል ሊሰጥ ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0973807293/0913971760 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ገነት ከተማ አለፍ ብሎ

 

የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት/ቱለፋ/

 

Save Tender