Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሽሮሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፈያ 500 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111-22-67-04
  • Website
  • Deadline13 Nov 2026, 4:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1 ብር 70,000፤ ሎት 2 ብር 56,000፤ ሎት 3 ብር 80,000፤ ሎት 4 እና 5 ብር 10,000፤ ሎት 6 እና 7 ብር 5,000 (CPO)
  • opening dateበማግስቱ 3:00 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Maintenance And Repair , Textile, Garment & Leather , Stationery Materials , Vehicle tire

በድጋሚ የወጣ የፅዳት፣ የቢሮ እቃዎችና ፅህፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልብስና ስፌት፣ ጎማ፣ የኮምፒውተር ጥገና እና የዲኮር ኪራይ ጨረታ (7 ሎት) - በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

  • ሎት 1 አላቂ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 70000.00 (ሰባ ሺህ ብር)
  • ሎት2 አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የፅህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 56,000.00 (ሃምሳ ስድስት ሺህ ብር)
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ ጨረታ ማስከበሪያ 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር)
  • ሎት4 የተሽከርካሪ ጎማ የመኪና ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • ሎት 6 የኮምፒውተር ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና ጨረታ ማስከበሪያ 5,000.00( አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት 7 የዲኮር ኪራይ ስራ ጨረታ ማስከበሪያ 5,000.00( አምስት ሺህ ብር)

በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በስማቸው ያላቸው የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ።
  2. ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200( ሁለት መቶ) በመክፈል ከፋይናንስ ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ኦሪጂናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተናጠል ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱን ስም ማህተም ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት። የሚጫረቱበትን እቃ አይነት በመጥቀስ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 የሥራ ቀናት በስራ ሰአት በቢሮ ቁጥር 14 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ባበቃ በመጨረሻው ቀን 10፡30 ሰዓት ይታሸግና በማግስቱ 3፡00 ሰአት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ/CPO/ ማስያዝ አለባቸው እና የጨረታው አሸናፊ 10% የጨረታውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. አሸናፊው ተጫራች ዘወትር በስራ ሰአት 2፡30 እስከ 11፡30 ንብረቶችን በራሱ በማጓጓዝ ማስጫኛውን እና ማውረጃውን ጨምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ማውረድ ይኖርባቸዋል።
  8. ፅ/ቤቱ የሚያጫርተውን እቃ ብዛት 20% መቀነስ መጨመር ይችላል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ መከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጫራቾች ማብራሪያ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0111-22-67-04 እና 011-80-12-02-40-04 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
  10. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ማቅረብ የማይችሉ ከሆነ ገላጭ አስፔሲፊኬሽን ማምጣት አልያም እቃውን የሚያሳይ ጥራት ያለው ፎቶ ማምጣት ይኖርበታል።
  11. ማንኛውም ተጫራች የመንግስት ግዥ አቅራቢነት ዝርዝር (SUPPLIER LIST) የተመዘገበ ሆኖ የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

አድራሻ፡- ሽሮ ሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፊያ 500 ሜትር ገባ ብሎ

በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Re-issued tender for 7 lots: cleaning supplies, office supplies/stationery, uniforms, vehicle tires, uniform sewing, computer/printer/photocopier maintenance, and decor rental. Bidders need a valid trade license, tax payment proof, TIN/VAT or TOT registration, and must submit samples or specifications.
Save Tender