በላፍቶ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ስረ የሚገኝ የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ህትመት ስራዎች፥ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ሌሎች ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሚጠገኑ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ስር የሚገኝ የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፡- 001/2018
በላፍቶ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ስረ የሚገኝ የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ህትመት ስራዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ሌሎች ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሚጠገኑ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች .............................................. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 21,000
ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች ..................................................... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 19,000
ሎት 3 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች .................................. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000
ሎት 4 የደንብ ልብስ ....................................................... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 22,343
ሎት 5 የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ ዕቃዎች ግዥ ........................ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,500
ሎት 6 የስፖርት እቃዎች .................................................. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,500
ሎት 7 የሚጠገኑ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች .......................... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,500
ሎት 8 የህትመት ስራዎች .................................................. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,000
በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ለእያንዳዱ ሎቶች ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቶች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 15 ስረ የሚገኝ ህዳሴ ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 37 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 37 ይከፈታል። የመክፈቻው ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 37 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 5 ፣ ለሎት 6፣ ለሎት 7 እና ለሎት 4 ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ለሎት 3፣ ለሎት 8 ማለትም ለቋሚ እቃ ት/ቤቱ የፍላጎት (specification) መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸንፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከገቢዎች ቢሮ 6 ወር ያላለፈው ክሪላንስ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 15 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ሃይሌ ጋርመንት ፊት ለፊት በሚወስደው አስፓልት ሀጫሉ ከፍ ብሎ ኦሮሚያ ኮንደሚኒየም ጀርባ።
ስልክ ቁጥር፡- 011-84-95368/011-84-90005
በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ስር የሚገኝ የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት
