በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን ሊሙ ገነት ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጽህፈት መሣሪያ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፣ የደንብ ልብሶች ፣ ሞተር ሣይክሎች ፣ የመንገድ ስራ ለመግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ሊሙ ገነት ከተማ አስተዳደር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን ሊሙ ገነት ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጽህፈት መሣሪያ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፣ የደንብ ልብሶች ፣ ሞተር ሣይክሎች ፣ የመንገድ ስራ ለመግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች ለእያንዳንዱ የግዥ መደቦች ሕጋዊ ነጋዴዎች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የጽህፈት መሣሪያ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ሞተር ሣይክሎች፣ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ስራ ለእያንዳንዱ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር 2017 የከፈለ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 10,000 (አስር ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፕኦ ወይም በካሽ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሠነድ ለእያንዳንዱ ማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የሊሙ ገነት ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ ዋጋ የአንዱን ነጠላ ዋጋ በመጥቀስ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ሁለት በተለያየ በታሸገ ፖስታ አድርገው አንድ ላይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሽያጭ የቀረበ እቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ አሸናፊው በራሱ ወጪ የመመለስ ወይም የመቀየር ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ተረን ኦቨር ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ ሌላ ሰነድ አሻሽሎ ወይም ለውጦ ማቅረብ አይችልም።
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ሕጋዊ የሆነ ካሽ ሬጅስተር በአግባቡ የሚጠቀሙ መሆናቸውን መረጃ የሚያቀርቡ አለባቸው።
- አንዱ ተጫራች በሌላኛው ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፋቸውን እንዳወቁ ያሸነፉበትን ዋጋ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ለሽያጭ ይቆያል፡፡
- ጨረታው 09/01/2018 ጀምሮ እስከ 29/01/2018 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በቀን 29/01/2018 በቀን 6:30 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8:00 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ሲመለስ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የግዢውን አጠቃላይ ዋጋ 10 (አስር በመቶ) የውል ስምምነት ሲፈረም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- በማይክሮ አነስተኛ እና መካከለኛ ማህበር የተደራጁት በመንግስት ግዥ ደንብ መሰረት ይበረታታሉ።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፉትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት ማንኛውንም ወጭ በራሱ ሸፍኖ እስከ ሊሙ ገነት ከተማ አስተዳደር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ሊሙ ገነት ከተማ አስተዳደር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
