Tender Detail

Tender Details


በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የጨፌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በአንደኛ ዙር የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮና የት/ት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ትምህርት ጽ/ቤት ጨፌ የመጀ/ደ/ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የጨፌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በአንደኛ ዙር የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮና የት/ት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

 

የሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

የብር መጠን

ሎት 1

የደንብ ልብስ

15,000,00

ሎት 2

አላቂ የት/ት እና የቢሮ ዕቃዎች

11,000.00

ሎት 3

የኤሌክትሮኒክስ እና የህንጻ ዕቃዎች

5,000.00

ሎት 4

የህትመት ሥራዎች

3,000.00

ሎት 5

የስፖርት ዕቃዎች

5,000.00

ሎት 6

የጽዳት ዕቃዎች

15,000.00

ሎት 7

ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ዕቃዎች አክሰሰሪዎች

10,000.00

ሎት 8

የቀይ መስቀል ዕቃዎች

5,000.00

ሎት 9

የላብራቶሪ ዕቃዎች

5,000.00

ሎት 10

የሙዚቃ መሳሪያ ዕቃዎች

6,000.00

ሎት 11

ፈርኒቸር

10,000.00

 

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፡፡
  4. ተጫራቹ በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው መሆን አለበት፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በጨፌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
  6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው 60 ቀን ብቻ ነው።
  7. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከት/ቤቱ የፋይናንስና ግዥ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 04 የጨረታ ሰነዱን /በየሎቱ/ ለ1 ሎት የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነጻ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍ እና ለሚያመርቱት ምርት/ዕቃ እንደ ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ ተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  8. አማራጭ የጨረታ ሃሳብ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ የመስሪያ ቤቱን ብረት ክፍል ድረስ ማስገባት እና ማስረከብ አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከነማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በታሸገ ፖስታ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ በቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡ ነገርግን 11ኛው ቀን በዓል የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ እና ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ዘግይተው ወይም በ11ኛው ቀን የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  14. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ እንደ ተገለጸለት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
  15. ተጫራቹ ባሸነፉበት የዕቃዎች ብዛት ላይ መስሪያ ቤቱ 20% ወደ ላይ 20% ወደ ታች አድርጎ መግዛት ይችላል፡፡ እንዲሁም ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከመገናኛ አያት ኮንደሚኒየም ቁጥር 1 ጸበል መድኃኒዓለም ፖሊስ ጣቢያ በታክሲ ተራ ገባ ብሎ ጨፌ የመጀ/ደ/ት ቤት ስልክ ቁጥር፡- 0116-39-18-17

 

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ትምህርት ጽ/ቤት ጨፌ የመጀ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender