በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ልማት ድርጅቶች ድጋፍና ክትትል ባለስልጣን የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በ 2017 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ ማስፈጸሚያ የሚውሉና ቀጥለው የተዘረዘሩትን እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Gosh Meda Pipe & Plastic Manufacturing Enterprise (የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት)
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ጨ/002/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ልማት ድርጅቶች ድጋፍና ክትትል ባለስልጣን የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በ 2017 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ ማስፈጸሚያ የሚውሉና ቀጥለው የተዘረዘሩትን እቃዎችን ማለትም፡-
|
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
|
1 |
የቢሮ አላቂ እቃዎችን (የጽህፈት መሳሪያዎችን) |
|
2 |
የደንብ ልብስና ተዛማጅ ቁሳቁሶችን |
|
3 |
የጽዳት እቃዎችን (ሌሎች አላቂ እቃዎችን) |
|
4 |
የቢሮ ቋሚ እቃዎችን (ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸርና ሌሎች) |
በብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የእቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ደሴ/ገራዶ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን / አገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ/ ቫቱን/ ጨምሮ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም።
- አንድ ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም። ሆኖም በሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ውስጥ አንድ ዕቃ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ ድርጅቱ ከጨረታ ውጭ የሚሆን ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን /ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 በመገኘት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ በይፋ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በየሎቱ ነው።
- ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ተወዳድሮ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ድርጅቱ ወደሚገኝበት ደሴ/ገራዶ አግሮስቶን ቅጥር ግቢ ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0962999933 / 0910607461 / 0920787579 0991841910 / 0923751571 በመደወል ወይንም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ደሴ/ ገራዶ አግሮስቶን ቅጥር ግቢ
የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት
