Tender Detail

Tender Details


በኮ/ቀ/ክ/ከ/ቀ/ጤ/ጣ/ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የቀራንዮ ጤና ጣቢያ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ቀ/ጤ/ጣ/ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት፤

ሎት 1 የደንብ ልብስ                             ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች

ሎት 3 የፅህፈት ዕቃዎች                          ሎት 4 ቋሚ አላቂ ዕቃዎች

ሎት 5 ቋሚ ዕቃዎች                             ሎት 6 የህትመት ሥራዎች

ሎት 7 የህንፃ ጥገና                               ሎት 8 የመኪና ኪራይ

ሎት 9 የኮምፒውተር ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና

በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ 10,000.00 ማስያዝ የሚችል፡፡

  • የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፡፡
  • የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የምትወዳደሩ የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ ከተደራጃችሁበት ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
  • አንዱ በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  • ተጫራቹ ሰነድ ለማስገባት ሲመጡ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  • የጨረታ ሰነዱ መሸጫ በየለቱ ዋጋ ብር 200.00 ነው።
  • ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 56 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4.00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ

  • ጤና ጣቢያው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ጤና ጣቢያው ለጨረታ አሸናፊው ውል ከመዋዋሉ በፊት 20% ወደ ላይ መጨመር 20% ወደታች መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተወደዳሪዎች ላሸነፉት ዕቃ ባስገቡት ናሙና መሠረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የሚቀርቡትን እቃዎችን በተቋሙ ጥራት ኮሚቴ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

አድራሻ

ከጦር ኃይሎች ወደ ቀራንዮ የሺ ደበሌ በሚወስደው መንገድ ወረዳ 08 ፅ/ቤት በስተጀርባ ቀ/ጤ/ጣቢያ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-38-39-040

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የቀራንዮ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender