የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጥራታቸውን የጠበቁ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን እና አገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018 በጀት ዓመት
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጥራቱን የጠበቀ እቃ ለመግዛት ስለፈለግን
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ እቃ፣ የሞተር ሳይክል ጎማ፣ የመኪና ባትሪ፣ ሴኩሪቲ ካሜራዎች፣ ካሜራ፣ ወንበሮች፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ ፣ ግራይደር ማሸን፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የልብስ ስፌት፣ ህትመት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ጥገና፣ ዲኮር፣ ድንኳን ኪራይ፣ ጫኝና አውራጅ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት እና የደረቀ ጭነት አገልግሎት ወዘተ የመሳሰሉት
- መስተንግዶ (የካፌ አገልግሎት) ለምትወዳደረ፡- በማኅበር የተደራጁ እናቶች መረጃ ያላቸው መሆን አለባቸው። ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እቃዎችን እና አገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እና የሚያስገቡት እቃ ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች ናሙና አቅራቢው በኮሚቴ ከተመረጠላቸው በኋላ ዓይነቱን የመቀየር፣ የማጭበርበር ወይም ጥራት የመቀነስ ሁኔታ ቢታይ ተመላሽ የሚደረግ መሆኑንና በተጨማረም በሕግ የሚያስቀጣቸው እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡
- ለወጣው ጨረታ በዘርፍ የተሰማሩ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቫት /ቲኦቲ/ ተመዝጋቢ የሆኑ ሠነዱን ሲያስገቡ ኦርጅናልና ኮፒው በማህተም የተደገፈና የባለቤትነት ሁኔታ ግልጽ የሚያደርግ ሌላ ሕጋዊ ተጨማሪ ማስረጃ ካለ በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በብር መጠን በየሎቱ እደሚከተለው በየሎቱ ማስያዝ አለባቸው
- ሎት1/ እስቴሽነሪ የብር መጠን 9,000 /ዘጠኝ ሺህ ብር/
- ሎት2/ የጽዳት እቃ የብር መጠን 17,500 /አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/
- ሎት3/ የደንብ ልብስ የብር መጠን 10,000 /አስር ሺህ ብር/
- ሎት4/ ቋሚ እቃዎች የብር መጠን 11,250 /አስራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር/
- ሎት5/ ህትመት ሥራ የብር መጠን 4,500 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/
- ሎት6/ መስተንግዶ የብር መጠን 21,000 /ሃያ አንድ ሺህ ብር/
- ሎት7/ የሕዝብ እና ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የብር መጠን 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/
- ሎት 8/ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት የብር መጠን 2,250 /ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር/
- ሎት 9 /ፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት የብር መጠን 1,000 /አንድ ሺህ ብር/
- ሎት 10 /የዲኮርና ድንኳን የማቅረብ አገልግሎት የብር መጠን 5,000 /አምስት ሺህ ብር/
- ሎት11 /ጫኝና አውራጅ አገልግሎት የሚሰጥ የብር መጠን 4,700 /አራት ሺህ ሰባት መቶ ብር/ በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለበት በአስረኛው ቀን 11:30 ላይ ታሽጎ ጨረታው በተጠናቀቀ ማግስት ወይም በአስራ አንደኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የእቃና የአገልግሎት ግዥ እንደማይሳተፉና ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታው ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት ወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ያልተሟላ ከሆነ ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከአዲሱ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ቀርበው መግዛት ይችላሉ ነገር ግን ሰነድ በነፃ የሚወስዱ ተጫራቾች የሚያጽፉት ደብዳቤ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ላይ እሴት የሚጨምሩበት መሆኑን ተገልፆ መጻፍ አለበት፡፡
- ማንኛውም ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በቀረበው የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግም ይሁን ማሻሻያ ማቅረብ ወይም ከጨረታው እራሱን ማግለል አይችልም፣ ይህ ሆኖ ከተገኘ በጨረታው ሕግ መሠረት የሚቀጣ መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ሲያስገቡ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:
09-21 69 89 15/ 09 22 22 45 26/ 09 12 24 48 66/ 09 47 15 78 63 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት ታክሲ ማዞሪያው ፖሊስ ጣቢያው ጋር እንገኛለን።
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናስ ጽ/ቤት
