Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
  • Address Lagar, Ras Mekonen Ave, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-551 24 00
  • Websitehttps://eic-et.com/branches/
  • Deadline17 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና
  • opening dateህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. በግዥ ዳይሬክቶሬት የስብሰባ አዳራሽ በ8:30 ሰዓት
  • Categories Printed Advertising Materials , Printing And Publishing

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከታች የተገለፁትን ብሮሸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።

Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ፋሀአዲ/ግዳ/003/2019

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከታች የተገለፁትን ብሮሸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።

ተ.ቁየህትመቱ ዓይነትብዛት
Amharic & EnglishAmharic & Afan OromoAmharic & Aaf Somali
1Takaful10,0007,0003,000
2Life Insurance13,0007,000
3General Insurance13,0007,000------

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ (Website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ፣ የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. በግዥ ዳይሬክቶሬት የስብሰባ አዳራሽ በ8:30 ሰዓት ይከፈታል::
  6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  7. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 217/262 ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Insurance Corporation seeks to print brochures (Takaful, Life Insurance, General Insurance) in Amharic-English, Amharic-Afan Oromo, and Amharic-Somali. Bidders must hold a valid business license, be registered on the government procurement supplier list, and provide VAT registration, TIN certificate, and tax clearance.
Save Tender