የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በሃገር ውስጥ ለሚፈጸሙ እቃዎችና ተዛማጅ አገልግሎቶች የሚውል ህትመት፤ የአላቂ የቢሮ እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ አላቂ የትምህርት እቃዎች፤ የጽዳት እቃዎችና ደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ለሚገዙ ዕቃዎች ለተጫራቾች የጨረታ መመሪያ ሰነድ የጨረታ ቁጥር፡-01/2017 በሃገር ውስጥ ለሚፈጸሙ እቃዎችና ተዛማጅ አገልግሎቶች የሚውል የሚዝዙ እቃዎች:- ህትመት፤ የአላቂ የቢሮ እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ አላቂ የትምህርት እቃዎች፤ የጽዳት እቃዎችና ደንብ ልብስ
- በመጀመሪያ ደረጃ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚችሉት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸው ወይንም ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ናቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ የዕቃው አይነት፤ የተመረተበት ዓመተ ምህረት፤ የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ፤ የአምራቹን ስም ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራቾች በየዘርፉ ንግድ ፈቃድ መኖር አለበት።
- ማንኛውም ተጫራቾች ዋናው የጨረታ ሰነድ ላይ በተጫራቹ የሚሞሉትን በመሙላት እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማኖር ሳይጨምር ሳይቀንስ መመለሰ ይኖርበታል።
- የጨረታ ፖስታ ዋናና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት። እነዚህም ሰነዶች የጨረታ አቅራቢው ድርጅት ወይም ህጋዊ ውክልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው።
- ተጫራቾች የእቃዎች ናሙና ከየአይነቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ የቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፊው ተጫራቾች ግን ናሙናዎች አይመለስም አንድ ተብሎ ይቆጠርለታል።
- ግገዢ ፈፃሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚመረጡብት ጊዜ የገዛውን እታ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነሰ ወይም ለመጨመር ይችላል።
- የመልካም አፈጻጸም ደብደቤ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ።
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ብቻ።
- የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-11፡00 ሰዓት ይሆናል። ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ10 /አስር/ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል። በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ወይም ሰነድ ላይ ሰማቸውን፣ ፈርማቸውን፣ አድራሻቸውን እንዲሁም ስልክ ቁጥራቸውን ማስፈር አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻል አለበት የሚሉ ጥያቄ ካላቸው የጨረታ ሰነዱ የመክፈቻ ጊዜ ሁለት ቀናት እስከሚቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ግዥ ፈፃሚ አካል ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሰነዱ መሸጫ ዋጋ 100 /አንድ መቶ/ ብር ብቻ።
- ማንኛውም ተጫራች ባስገባው ጨረታ ሲፒኦ ማስያዣ ዋጋ ሎት 1 - 8,000 ለፕላንትና ማሽነሪ እቃዎች፣ ሎት 2 - 8,000 ለህንጻና ቁሳቁስ እቃዎች፣ ሎት 3 – 7,000 ለት/ት እቃዎች፤ ሎት 4 – 3,000 ለደንብ ልብስ፤ ሎት 5 – 7,000 ለሌሎች አላቂ እቃዎች፣ ሎት 6 – 2,000 ለህክምና እቃዎች ሰነዱ በራሱ አንድ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ ከተዘረዘሩት እንድም ነገር እንኳን የማያሟላ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- የርክክብ ቦታ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እቃው ለንብረት ክፍል ካስገባና ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያው ይፈጸማል፡፡
አድራሻ፡- አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ከኢትዮጰያ ሜትሮሎጂ ኢንስትዩት ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
