Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ወለጋ ዞን የሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም ለሆማ ወረዳ የተለያዩ ጽ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ አላቂ እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ የመኪና ጎማዎች፤ የግንባታ ዕቃዎች እና ደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሴክተር መስሪያ ቤቱ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን የሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆማ


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ወለጋ ዞን የሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም ለሆማ ወረዳ የተለያዩ ጽ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ አላቂ እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ የመኪና ጎማዎች፤ የግንባታ ዕቃዎች እና ደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሴክተር መስሪያ ቤቱ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ እና በተወዳዳሪዎች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

የጨረታ መስፈርቱ፤

  1. ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
  2. በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ
  3. የ2017 ዓ/ም ግብር አጠናቀው የከፋሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታክስ ከፋይነት (TIN) የተመዘገቡ እና ተጨማሪ ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
  4. ለጨረታ ማስከባሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 2% በተረጋጋጠ (CPO) ከማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት (15) የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር (200) በመክፈል ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ፤
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዛው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
  7. ተጫራቾች የሚወዳዳሩበት የዕቃ ዓይነት የቢሮ ዕቃ መሆኑን እንደዚሁም የድርጅቱን ስም በሚያቀርቡ የተለያየ ፖስታ ላይ በኦሪጅናሉ እና በኮፒው በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ማሕተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፣
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተለያየ ኢንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  9. ተወዳዳሪዎች ናሙና እንድያቀርቡባቸው የተጠየቁትን ሙሉ በሙሉ ማቅረብ እና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቆጥሮ ማስረከብ አለባቸው፤
  10. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድሰተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
  11. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፤
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-17-08-05-60 ወይም 09-17-35-64-32 መጠየቅ ይችላሉ፤
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በምዕ/ወለጋ ዞን የሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender