በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጐሮ ሙጢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት አመት በስሩ ባሉት መስሪያ ቤቶች የሚያስፈልጉ የቢሮ ቋሚ እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች ፤ የተለያዩ የቢሮ አላቂ እቃዎች ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ የደንብ ልብስ ፤ የቴክኒክ እና ሙያ እቃዎች ፤ የመኪና እና የሞተር ሳይክሎች ጎማዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጐሮ ሙጢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጐሮ ሙጢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት አመት በስሩ ባሉት መስሪያ ቤቶች የሚያስፈልጉ ለቢሮ እቃዎች የሚውሉ፡-
የቢሮ ቋሚ እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች ፤ የተለያዩ የቢሮ አላቂ እቃዎች ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ የደንብ ልብስ ፤ የቴክኒክ እና ሙያ እቃዎች ፤ የመኪና እና የሞተር ሳይክሎች ጎማዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩበት ሥራ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ከፍለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰምና ማህተብ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የግብር ከፋይነት ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 15 ፐርሰንት (ቫት) ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ ወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ማድረስ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) ብር ብቻ በመክፈል በጎሮ ሙጤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በዚህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ማስከበሪያ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) ሲፒኦ በቢሮ ሥም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ሀ. ጨረታው አሸናፊ ከተባለበት ቀን እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል።
ለ. ለተወዳዳሪ ዝርዝር ዋናውን በቀረበለት ሰነድ ላይ መሙላት ይኖርበታል።
ሐ. ተወዳዳሪው የእቃውን ዝርዝር ሲቀርብለት የተመረተበትን ሃገር እና አይነት መጥቀስ አለበት፡፡
መ. የጨረታው ሰነድ ሲሞላ የቃላት ለውጥ፣ ስረዝ ድልዝ ካለበት ተቀባይነት የለውም፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 09-05-68-98-56/ 09-26-71-25-26
ጐሮ ሙጢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
