በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጽሕፈት መሳርያ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ፈርንቸሮች
- የሠራተኛ ደንብ ልብስ
- የመኪና ጎማና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
- የኮንስትራክሽን እቃዎች
- የበሬ ቄራ ማሽነሪ
በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ንግድ ፍቃድና በሕጉ መሠረት ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፤
- የአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (መቶ) ብር በነንሰቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደር ሃሳባቸው ላይ በመ/ቤታችን በተሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም ፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 8 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ናሙና መታየት የሚገባውን ዕቃዎች በናሙናና በፎቶግራፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት የተጠበቀና በተሰጠው እስፔስፍኬሸን መሠረት ኦርጅናል ዕቃ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ጥራቱ ያልተጠበቀና አረጅናል ያልሆነ ዕቃ ካቀረበ መመለስና መቀየር ግዴታ ይኖርበታል፣
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የተጠየቀው እቃዎች ሞዴል በተጠየቀው እስፔስፊኬሺን መሠረት ተሞልቶ ካልቀረበና ማንኛውም ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የድርጅቱ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተራ ቁጥር 1. 10,000 ፣ በተራ ቁጥር 2.10,000፣ በተራ ቁጥር 3. 8000፣ በተራ ቁጥር 4.10,000 ፣ በተራ ቁጥር 5. 20,000 ፣ በተራ ቁጥር 6. 10,000 በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ብር በነንሰቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ አለበት፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን- 14/12/2017 በሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው የሥራ ቀን 15/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 8 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላላፈው ውሳኔ ተገዢ ይሆናሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታዉን ትቻለው ማለት አይችልም፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች መ/ቤቱ በሚሰጠው የአቅርቦት ትዕዛዝ መሠረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ እና በመ/ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡ 0913265326, 0910376599 ፣ 0939606274፣ 0908303549 እና 0917514081 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
