Tender Detail

Tender Details


የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት፣ የፅዳት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ደንብ ልብስና የጥገና እቃዎች ግዥ

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 - ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች...... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 2 - መጋረጃና ምንጣፍ .........የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 3 - የፅህፈት መሳሪያዎች ..........የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 4 - ሕትመቶች.. .........የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 5 - የፅዳት ዕቃዎች....... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 6 - የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት ......የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 7 - የተሽከርካሪ ጎማ እና ባትሪ ..............የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 8 - የተሽከርካሪ መለዋወጫ እና ጌጣጌጥ ..............የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 9 - የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና............ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 10 - የተሽከርካሪ መለዋወጫ.................. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 11 - የሠራተኞች ደንብ ልብስ /ጨርቅ/ .........የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 12 - የሠራተኞች ደንብ ልብስ /ጫማ/....የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት 13 - የመብራት የጥገና እቃዎችና የዕጅ መሳሪያዎች ....የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00 በማስያዝ፤
  • ሎት -14 የውሃና የሳኒቴሽን ጥገና እቃዎች ....የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 በማስያዝ፤

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት /ማስራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ወይም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤ እና የሚገዛው ዕቃ እና ተያያዥ አገልግሎት ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የዘመኑን የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ቀናት ከሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 27 የዕቃዎችን ዓይነት፣መጠንና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ከተ.ቁ እስከ 14 የተዘረዘሩትን የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር በመክፈል ከሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ ቤት ግዥ ፋይ/ ንብ/ አስተዳደር ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 27 መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃና አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በቀረበው ዝርዝር መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) የቀረበ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  6. በእያንዳንዱ ሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ መሙላት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል። ሁሉም እቃዎች መሙላት አለባቸው።
  7. በጨረታ ሰነዱ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ስርዝ ድልዝ ካለው ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በየሎቱ በመለየት በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም በሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ን/ብ/ አስተዳደር ቡድን 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 27 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጠዋቱ 3:30 ማስገባት / ማቅረብ/ ይኖርባቸዋል፤ ከጠዋቱ በ3:30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም የጨረታ ሰነዳቸው ተሟልቶ ከቀረበ ባይገኙም በይፋ ይከፈታል።
  9. ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቁትን ዕቃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ወይም ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  12. ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ ከሚፈፅመው ክፍያ ላይ ደረሰኝ በመስጠቱ 3% የቅድመ ክፍያ ታክስ /with-Holding Tax/ ታክስን እና በግዥው ተይዞ ስለሚከፈል የቫቱን 50% ወይም 7.5% ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ዊዝሆልዲንግ) ይዞ የማቆየት መብት አለው።
  13. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-681-14-59 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት/ደብረ ብርሃን

Summary
North Shewa Zone High Court (Debre Birhan) invites bids in 14 lots including electronics, curtains and carpets, stationery, printing, cleaning items, vehicle parts, tyres, lubricants, staff uniforms and maintenance items.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender