Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት ዕቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ እና የቢሮ ፈርኒቸር በ3 ሎት ለመግዛት ያወጣው ግልጽ ጨረታ (ቁጥር 01/2019)።

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለጽህፈት መሳሪያና የጽዳት ዕቃ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ ከህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት (Lot 1) የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃ
  • ሎት (Lot 2) ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ
  • ሎት (Lot 3) የቢሮ ፈርኒቸር

በዚሁ መሰረት፡፡

  1. 2019 ዓ/ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  2. አግባብ ካለው የመንግስት ተቋሚ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ሴርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና ተጨማሪ ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለጽህፈት መሳሪያና የጽዳት ዕቃ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ በህጋዊ ተጫራቾች ከአሰሪና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ማግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. ተጫራቾች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  5. አንድ ተጫራች ከአንድ ሠነድ በላይ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሦስቱም ሎት (Lot) (100,000) አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ወይም የክፍያ ማስያዥ (CPO) ከማረጋገጫ ሠነድ ጋር ማቅረብ ሚችል/ትችል፡፡
  7. ተጫራቾች በመመሪያ መሠረት ህጋዊ ፍቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገበበት ሰርተፍኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአሥር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር ለሦስቱም ሎት (Lot) 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ግቢ ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 309 ሦስተኛ ፎቅ በመክፈል ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታው ሠነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ሠነዱን ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናልና ኮፒ ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ሠነዱ በተለያዩ ፖስታና ኤንቬሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በመጨመር በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (11ኛው) ቀን ከጠዋቱ 4:00-4:30 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት 4:30 ይታሸጋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ የዛኑ እለት 5:00 ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
  11. ገዥ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

Summary
Sidama Regional Police Commission buys, in 3 lots, stationery and cleaning supplies, electronics, and office furniture. Bidders need a 2019 E.C. renewed licence, TIN, VAT, tax clearance and a competence certificate.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender