የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል (ኢግምኢ) የቢሮ ጽህፈት፣ የጽዳትና የመስክ መገልገያ ዕቃዎች፣ ማዳበሪያና ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች፣ የላብራቶሪ ኬሚካሎች፣ የግንባታ ዕቃዎችና ቋሚ የቢሮና ላብራቶሪ ዕቃዎችን በ7 ሎት ለመግዛት ያወጣው ግልጽ ጨረታ (ግጨቁ 01/2019)።
Jimma Agricultural Research Center (የጅማ የግብርና ምርምር ማዕከል)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ግጨቁ 01/2019
የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል ከዚህ በታች የተገለጹትን ማለትም፡-
- ሎት 1. አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎችና አነስተኛ የእጅ መገልገያ መሣሪያዎች
- ሎት 2. አላቂ የመስክ መገልገያ መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 3. አነስተኛ የመስክ የእጅ መገልገያ መሣሪያዎች
- ሎት 4. የግብርና ግብዓቶች የአፈር ማዳበሪያ፣ የተባይ መከላከያ ኬሚካልና የአረም መድኃኒቶች
- ሎት 5. አላቂ የላብራቶሪ ኬሚካሎች
- ሎት 6. አላቂ የግንባታ መገልገያ ዕቃዎችና ተያያዥ ቁሳቁሶች
- ሎት 7. ቋሚ የቢሮና የላብራቶሪ መገልገያ ዕቃዎች
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (Tin Number) ሰርተፊኬት ያላቸውና
- በመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይና በ(Web Site) የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በአካል በመገኘት በመግዛት ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል ስም በማስያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መልኮ በሚገኘው የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል የግዥ የስራ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡ የአሸናፊዎች የዕቃ ማስረከቢያ ቦታ መልኮ በሚገኘው ዋና ማዕከል መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መልኮ በሚገኘው የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ታህሳስ 06 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
በበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥር 0474525561/0911749116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
