Tender Detail

Tender Details


የቦንጋ ማረሚያ ተቋም ለ2019 በጀት ዓመት የምግብ ማጣፈጫ፣ የቢሮ ጽሕፈት፣ የጽዳት፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የግንባታ ቁሳቁሶች፣ ኤሌክትሮኒክስ (ኮምፒዩተሮች)፣ የሙያ ስልጠና ቁሳቁሶች እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ በ8 ሎት ለመግዛት ያወጣው ግልጽ ጨረታ።

ቦንጋ ማረሚያ ተቋም

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የቦንጋ ማረሚያ ተቋም በ2019 በጀት ዓመት ለሕግ ታራሚዎች መና ዝግጅት ለመንግሥት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ፡-

  1. የምግብ ማጣፈጫ ቁሳቁሶች
  2. አላቂ የቢሮ ጽሕፈት መሣሪያዎች
  3. የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች
  4. የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች
  5. የግንባታ ቁሳቁሶች
  6. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /ኮምፒዩተሮች/
  7. የሙያ ስልጠና ቁሳቁሶች
  8. የሠራተኞች የደንብ ልብስ

ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ነጋዴዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
    • በዘርፉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
    • በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የዘመኑን የመንግሥት ግብር በመክፈል ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ሆኖ ኦርጅናል ንግድ ፈቃድ አቅርቦ ማመሳከር የሚችል፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር CPO/ ማስያዝ የሚችል፡፡
  3. ለምግብ ማጣፈጫ ቁሳቁሶች የውል ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር CPO/ ማስያዝ የሚችል፡፡
  4. ለሌሎች ቁሳቁሶች የውል ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር CPO/ ማስያዝ የሚችል፡፡
  5. በራሱ ትራንስፖርት እስከ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢ ማድረስ የሚችል፡፡
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት/ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሠረት ዋጋ ገልጸው በታሸገ ፖስታ እስከ 15ኛ የሥራ ቀናት ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጨረታው በ15ኛ ቀን 11:30 ሰዓት ይታሸግና በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በማረሚያ ግቢ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  • ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡

የቦንጋ ማረሚያ ተቋም

Summary
Bonga Correctional Institution buys, in 8 lots, food seasonings, office stationery, cleaning items, office furniture, construction materials, computers, vocational training materials and staff uniforms. Suppliers deliver to the prison compound.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender