Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሀዲያ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913609885
  • Website
  • Deadline04 Dec 2026, 5:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 5000 (CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ)
  • opening date11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30
  • Sector Office Supplies And Services , Stationery Materials

የሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የጽህፈት መሣሪያ ግዥ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽ/መሣሪያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ:-

  1. በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው
  3. ምዝገባ የምስክር ወረቀት ሠርተፍኬት ያለው
  4. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
  5. ሌሎችም ማስረጃዎች ካሉ በማያያዝ ማቅረብ የሚችልና ዕቃውን ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ ድርጅቱ ከሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል መግዛት ይችላሉ::

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን 5000/አምስት ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) /በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸውና የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ከላይ የተገለጸውን ማስረጃዎች ጭምር በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁ.14 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል:: የሚቀርበው ዋጋ የመንግሥት ክፍያን ያካተተ መሆን አለበት::ጨረታውም 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 2:30 ይከፈታል:: የተሞላው ዋጋ በአሃዝ የማይነበብ ከሆነ በፊደል የተጻፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በዕለቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂዳት አያስተጓጉለውም::

ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

በሀድያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Summary
Lemo Woreda Finance and Economic Development Office (Hadiya Zone) invites open bids to supply assorted stationery, delivered to the office.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender