Tender Detail

Tender Details

  • Company Hawassa University Income Generating Enterprise (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ)
  • Address Hawassa University main campus, Policy Development and Research Institute building, 1st floor, Hawassa, Phone: 0924388128
  • Website
  • Deadline09 Dec 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለሁሉም ሎት ብር 200,000 በጥሬ ገንዘብ፣ የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO
  • opening dateበዚያው ዕለት 4:00 ሰዓት
  • Sector Food And Beverage , Food Items And Drinks

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የባልትና ውጤቶች፣ እህልና ጥራጥሬ፣ የታሸጉ ምግቦች፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ሌሎች የምግብ ግብዓቶችን ለመግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ።

Hawassa University Income Generating Enterprise (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለሆቴል አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን ለመግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለሆቴል ሥራ አገልግሎት የሚሆን የባልትና ውጤቶች፣ እህልና ጥራጥሬ፣ የታሸጉ ምግቦች እና ሌሎች ተዛማጅ ግብዓቶች እና አትክልትና ፍራፍሬ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች/ግለሰቦች ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ የተመዘገበ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ በፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ላይ ከሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቀርበው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሁሉም ሎት የጨረታውን ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የተሟላ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሠነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስተኛ ቀን ጠዋት 3:30 ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ጨረታ ሳጥን ውስጥ ካስገቡ በኋላ በዚያው ዕለት 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው ውጤት የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንደተጠናቀቀ የሚገለጽ ሲሆን በቴክኒክ ግምገማው ያላለፈ ተወዳዳሪ ለፋይናንሻል ውድድር አይቀርብም፡፡
  8. የጨረታ ውድድሩ ሂደት እንደተጠናቀቀ የግዥ ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ በኩል ለተወዳዳሪዎች ባስመዘገቡት አድራሻ አማካይነት ይገለጽላቸዋል፡፡
  9. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ዋና ጽ/ቤት፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ወይም ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሚገኝበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0924388128/0916515716/0993917804 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ

Summary
Hawassa University Income Generating Enterprise buys food supplies for its hotel service: processed household foods, grains and pulses, packaged foods, vegetables and fruit, and related inputs. Bidders need a renewed licence, TIN and VAT registration.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender