Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline15 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ግዥ ብር 25,000.00 (CPO ብቻ)
  • opening dateጠዋት በዕለቱ 4:30
  • Sector Food And Beverage , Printing And Publishing

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት የዓመታዊ መጽሔት ህትመትና የባህላዊ ጠጅ አቅርቦት ግዥ

SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ለመጀመሪያ ጊዜ እና በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ እቃ ግዥ /አገልግሎት/ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም፡-
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጣ የዕቃ/ የአገልግሎት/ ግዥ
ሎት 1 ዓመታዊ የመጽሔት ህትመት
ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጣ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ
ሎት 2 የባህላዊ ጠጅ አቅርቦት ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2018/2019 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣የግብር ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡
  7. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
  8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 06 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4:30 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባ አለባቸው፡፡
  11. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ለሎት 1 ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ናሙና ወይም እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) እንደዚሁም ለሎት 2 ቴክኒካል ድርጅታዊ ብቃት እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት 60% እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት 40% ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ፣ የናሙና ግምገማ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/0115 15 73 37

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

Summary
Filwuha (Spa) Service Enterprise invites bids for annual magazine printing (lot 1, first call) and traditional tej (honey wine) supply (lot 2, second call).
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender