የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና እቃዎች፣ ጎማና ዘይት ግዥ
የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ሪጅኦፖሊታን ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤትና ለሌሎች ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት1 የጽህፈት መሳርያ ፣ ሎት 2.የጽዳት እቃ ሎት፣ 3. ቋሚ እቃ/ ፈርኒቸር፣ ሎት4. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5 ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ጎማ፣ ሎት 7 የመኪና ዘይት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በቀን 6/03/2019 ዓ.ም የወጣዉን ጨረታ በማየት ሰዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ከብር 500,000 / አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1- 7 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ጨረታ መከፈቻ ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው ።
- ተጫራቾች ከሎት1 - ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸዉ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ብቻ የጠቅላላ ዋጋን 1 ፐርሰንት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር /ብቻ በኮ/ቻ ከተማ ቦርከና ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት በመክፈል ከቀን 06/03/2019 ዓ.ም እስከ 15/03/2019 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰአት እስከ 11:30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በቦርከና ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን06/ 03/2019 ዓ.ም እስከ 15/03/2019 ዓ.ም 11:30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በቀን 16/03/2019ዓ.ም ከጠዋት 4 :00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል ። ይሁን እንጅ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል ።
- አስፈላጊ ለሆኑ እቃዎች ክፍለ ከተማው ሳንፕል የሚያቀርብ በመሆኑ ሳንፕሉን በጥንቃቄ በማየት እቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ወጪ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪ መስሪያቤት ጋር ከጨረታው መከፈቻ ከ5 አምስት ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0920208544 /0921257510 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል። ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ45 ቀናት ይሆናል።
- ጨረታውን ለማባዛት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ እና ለወደፊቱም ለመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።
- ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20 ፐርሰንት (ሀያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ቦርከና ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኮምቦልቻ ሪጅኦፖሊታን ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Borkena Sub-City Administration Office (Kombolcha city) invites bids in 7 lots: stationery, cleaning items, furniture, electronics, vehicle consumables, tyres and lubricants. National open bid.
