የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ድርጅት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የFM ሬድዮ ትራንስሚሽንና ሶላር ጄኔሬተር እና የመኪና ጎማዎች ግዥ
የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች
ሎት: 01 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኮምፒዩተር ቪድዮ ካሜራ እና ፎቶ ካሜራ አክሰሰሪዎች
ሎት 02 FM Radio Transmission እና ሶላር ጄኔሬተር /solar battery and panel
ሎት 03 የቢሮ መኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይጋብዛል
- ከላይ የተጠቀሰ ዕቃ ቀጥታ ግንኙነትና አግባብነት ያላቸው የዘመኑን ወይም የ2018 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፣እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት እና የቫት / የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎት01፤ሎት02 እና ሎት03 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ድርጅት ገንዘቡን በመክፈል ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን በቢሯችን G+2 ሕንፃ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰነድ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ድርጅት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/ አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል ።
- 16ኛው ቀን የመንግሥት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በደቡብ ምዕራብ ኢ/ያ/ሕ/ክ/መ/ ሸካ ዞን በማሻ ከተማ የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ድርጅት ማቅረብ አለበት።
- ውል እንዲገባ ከተጸፈበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ዕቃዎችን በራሱ መጓጓዣ ማዘጋጀት / ማቅረብ/ አለበት።
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
- የሚቀርቡ እቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጣቸው ስፔስፍኬሽን መሰረት አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0475580788፣0912940077 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Sheka Community Television and Radio (Masha, South West Ethiopia) invites bids in 3 lots: electronics including computers and cameras, FM radio transmission and solar generator, and office vehicle tyres. Open bid.
