Tender Detail

Tender Details

  • Company በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ስር የሚገኘው የወረዳ 11 ጤና ጣቢያ
  • Address ን/ስ/ላ/ከ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ ልዩ ስም ሀና ማሪያም ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-47-11974
  • Website
  • Deadline24 Nov 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 400.00 ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid Securityየግዥውን 1(150,000) (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ)
  • opening dateበሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት፣ በጤና ጣቢያው
  • Categories Maintenance And Repair , Printing And Publishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Medical Equipment And Supplies , Stationery Materials , Cloth And Shoes

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት፣ የጽዳት፣ የህክምና እቃዎች እና የጥገና፣ ህትመትና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ግዥ (2ኛ ዙር)

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ስር የሚገኘው የወረዳ 11 ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ስር የሚገኘው የወረዳ 11 ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎችና ስራዎች በ2ኛ ዙር ን/ስ/ወ 11/002/2019 ዓ.ም ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። እነሱም የደንብ ልብስ፤ አላቂ የጽህፈት እቃዎች፤ የጥገና እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ የጥገና ስራ፤ የህትመት ስራ፤ ሻይ ቡና፤ የኮምፒዩተር ጥገና፤ የፕሪንተር ጥገና ፎቶ ኮፒ ጥገና የጽዳት እቃ፤የደንብ ልብስ ስፌት የመጋረጃ ስፌት ፤ የጭነት አገልግሎት(የመኪና ጭነት) የመድሃኒት እና የህክምና እቃዎች መግዛት ይፈልጋል። ሆኖም ተጫራቾች እቃው በአስቶር ውስጥ ስለመኖሩ ወይም የቴክኒክ ባለሙያዎች መጥተው ማየት ሲፈልጉ እንደሚያቀርቡ ማረጋገጫ ደብዳቤ መስጠት የሚችሉ መሆን አለባቸው። ሆኖም ግን የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ:

  1. ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ ግብር የተከፈለበት እና የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ፣
  2. በመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የእቃ አቅራቢወች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ቫት/ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እንዲሁም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ከአደራጀችው አካል ደብዳቤ እና ደብዳቤው ሼድ እንዳላቸው የሚገልጽ መሆኑን አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት ተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ዘወትር በስራ ሰዓት 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይኖርባችኃል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዝርዝርና ዋጋ እና መለያ ቁጥር ከላይ ከተጠቀሰው ተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማህተምና ፊርማ በማኖር ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ አራተኛ ፎቅ በግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ውስጥ ባለው በታሸገ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. በመክፈቻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታውን ሳጥን መክፈቻ ስነስርዓት አያስቀርም።
  7. ፋይናንሻል እና እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል ብሎ በመለየት በአንድ ፖስታ በማሸግ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ:- የግዥውን 1(150,000) (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ)
  9. የጨረታ ሳጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ሰዓት ታሽጎ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4:00 ሰዓት በጤና ጣቢያው ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል መ/ቤቱ ናሙና ራሱ አቅርቦ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለእይታ አስቀርቦ በናሙና መሰረት እንዲያቀርቡ የሚያደርጋቸው ግዥዎች መኖራቸውን እንዲታወቅ፡ : የሚቀርቡ ናሙናዎች ብዛት በዋጋ ሰነድ ላይ ይመልከቱ የሚቀርቡበት ጊዜ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ሲሆን የሚቀርቡት ክፍል ራሱ በተዘጋጀው ክፍል ነው።
    ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና በሚመረመርበት ወቅት በእቃው ባህሪ ምክንያት ቢበላሽ ቢጠፋ ካሳ አይከፈለም። ውጤት ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ6 ወር ውስጥ ካልወሰዱ በውርስ ለመንግስት ገቢ የሆናል።
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. መደበኛ የጨረታ ሰነድ (SBD) ከተቋሙ የተወሰዱትን አንብቦ እና የተሞላ አድርጎ ሙሉ በሙሉ የጨረታ ሰነዱን መመለስ /ማስገባት / ይኖርባቸዋል።

የመስሪያ ቤቱ አድራሻ
ን/ስ/ ላ/ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ሀና ማሪያም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት።
ለበለጠ መረጃ :- የስልክ ቁጥር:-011-47-119-74

የን/ስ/ ላ/ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Nifas Silk Lafto Sub-City Woreda 11 Health Center (2nd round) seeks suppliers of uniforms, stationery, maintenance items, fixed assets, cleaning items, medicines and medical supplies, plus maintenance, printing, tailoring, catering and transport services.
Save Tender