በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የወረዳ 06 አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ የመድሀኒት፣ የህክምና እቃዎች፣ ጥገና፣ ህትመት፣ የመኪና መለዋወጫና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ግዥ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 06 አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር ARHC 002/2019 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 06 አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1- መድሀኒት እና የህክምና እቃዎች.................50000
ሎት 2 የቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች.................5000
ሎት 3 የመድሀኒት ማስወገድ አገልግሎት.................3000
ሎት 4 ዲጂታል ህትመት................................ 4000
ሎት 5 የመኪና መለዋወጫ እና ጎማ.................. 20000
ሎት 6 የሰራተኛ ካፌ.............5000
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ማሟላት የሚገባችሁ መስፈርቶች።
01:- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው የሚቀርብ ማስረጃ
02:- የመንግስት የግዢ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
03:- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
04:- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 መግዛት ይችላሉ።
05:- የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
06:- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውላል።
07:- ተጫራቾች የዶክመንታቸውን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ውል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
08:- ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።
09:- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ እንደተነገራቸው ቀርበው ውላቸውን ለመፈጸም 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10:- ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11:- ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ዋጋ ቫትን ጨምረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12:- የጨረታ ሳጥን የሚዘጋው ጨረታው በወጣ 11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4.30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
13:- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ መመለስ ይኖርባቸዋል።
14:- ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ማህበራት በመመሪያው መሰረት በሚሰሩት ምርት ወይም ግብአት ላይ ብቻ ሰነድ ያለክፍያ መውሰድ ወይም መጫረት ይችላሉ።
15:- ጤና ጣቢያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ /ቤት አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ በተለምዶ ጫካ ሜዳ በሚባለው ሜይዴይ ትምህርት ቤት ገባ ብሎ ነባር ቀበሌ 32።
ስልክ ቁጥር 0112786801/ 0112758961
