Tender Detail

Tender Details


በሱሉልታ ወረዳ ጫንጮ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የሠራተኞች የደንብ ልብስና ስፌት፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የሕክምና መድሃኒቶች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የአምቡላንስ ጎማ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና የፕሪንተር ቀለም ሙሌት እና ቋሚ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

በሱሉልታ ወረዳ ጫንጮ አጠቃላይ ሆስፒታል


የጨረታ ማስታወቂያ

በሱሉልታ ወረዳ ጫንጮ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ በ2019 የበጀት ዓመት የሚገዙ የዕቃ ዝርዝሮች

  1. የሠራተኞች የደንብ ልብስ አቅርቦት
  2. የሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት
  3. የጽህፈት መሣሪያዎች
  4. የሕክምና መድሃኒቶች
  5. የጽዳት ዕቃዎች
  6. የአምቡላንስና ፒክ አፕ ጎማ ግዥ
  7. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገ፣ የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለም ሙሌት
  8. ቋሚ እቃዎች

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም ዕጩ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  • ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው። የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 ( ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከጫንጮ ሆስፒታል መግዛት የምትችሉ
  • በሚወዳደሩበት ዕቃዎች ከጨረታ ሰነድ ጋር ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ የሚችሉ
  • የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ 10,000 ብር ( አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ( C.P.O) ማቅረብ የምትችሉ።
  • በተጠየቀት ዕቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ያላቀረበ ተወዳዳሪ ከጨረታው ይሠረዛል
  • ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በወጣው በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሱሉልታ ወረዳ በጫንጮ ሆስፒታል ይሆናል ።

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- በሰሜን ሸዋ ዞን ጫንጮ አጠቃላይ ሆስፒታል
ስልክ ቁጥር 0111881024 /0111880953/0913247067

በሱሉልታ ወረዳ ጫንጮ አጠቃላይ ሆስፒታል

Summary
Chancho General Hospital (Sululta Woreda, North Shewa, Oromia) buys staff uniforms and tailoring, stationery, medicines, cleaning items, ambulance and pickup tyres, electronics repair and toner refilling, and fixed assets. Bidders need a renewed licence and must submit samples.
Save Tender