Tender Detail

Tender Details

  • Company African Center Early Childhood Development
  • Address , Phone: 0911152603
  • Website
  • Deadline30 Nov 2026, 2:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityብር 50,000 (ሃምሳ ሺ) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና (Bank Guarantee)
  • opening dateኅዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም. 8:30፣ በማዕከሉ ኤሻል ታወር፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢ.ሮ 201 ጨረታው በይፋ ይከፈታል።
  • Categories Printing And Publishing , Graphic Design

የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል (AfC-ECD) ለአንድ ዓመት በኮንትራት ውል የግራፊክ ዲዛይንና ኢላስትሬተር አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ያወጣው ማስታወቂያ (Afc-ECD/Gov/LB/PC-11/2026)።

African Center Early Childhood Development


የጨረታ ግብዣ ማስታወቂያ

የግራፊክ ዲዛይንና ኢላስትሬተር ግዥ
የጨረታ ቁጥር:- Afc-ECD/Gov/LB/PC-11/2026

የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል (AfC-ECD) ለተቋሙ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራሞችና ለተቋማዊ የግንኙነት ሥራዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ የግራፊክ ዲዛይንና ኢላስትሬተር ፍላጎቶች ስላሉ፣ አገልግሎቱን የሚሰጥ ድርጅት ለረዥም ጊዜ (አንድ ዓመት) በኮንትራት ውል በመቅጠር ለማሠራት ብቁና በዘርፉ ተዛማጅ የሥራ ልምድ ያላቸውን አማካሪዎች ለጨረታ ይጋብዛል። የውሉ ጊዜ ከታኅሣሥ 23 ቀን 2019 እስከ ታኅሣሥ 21 ቀን 2020 ዓ.ም. ይሆናል።

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ በአድራሻችን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል፣ ጎተራ ወንጌላዊት ሕንፃ አጠገብ በሚገኘው ኤሻል ታወር፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201 በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ፤
  2. ተጫራቾች በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ ማስገቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ
  3. ኅዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም. 8:30፣ በማዕከሉ ኤሻል ታወር፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢ.ሮ 201 ጨረታው በይፋ ይከፈታል ፤ የጨረታውንም ሂደት በአካል በመገኘት መከታተል እንደምትችሉ እናሳውቃለን።

1. የሥራው ዓላማ

የዚህ የአገልግሎት ግዥ ዋና ዓላማ በቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ዙሪያ ለማስተማሪያ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዶችን፣ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ማስተዋወቂያ ቁሳቁሶችን፣ ዓመታዊ ዕቅዶችንና ሪፖርቶችን፣ መጽሔቶችን፣ የአካዳሚክና የምርምር ውጤቶች፣ የዜና መጽሔቶችን (news letter)፣ የፖሊሲ ማብራሪያ ሰነዶችን፣ የሥልጠና መመሪያዎችን፣ የአሠራር ማኑዋሎችንና ሌሎች የተቋሙን ኅትመቶች ለሕትመትና ለዲጂታል ሚዲያ በሚስማማ መልኩ የሥዕልና የግራፊክ ዲዛይን ማዘጋጀት ነው።

2. የተጫራች ድርጅት ብቃትና ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  • የትምህርት ደረጃ:-ተቋሙ ለዚህ ሥራ የሚመድባቸው ባለሙያዎች ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው ዘርፍ ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፣ ተዛማጅ የሥራ ልምድና ሙያዊ ማረጋገጫ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • የሥራ ልምድ:- በግራፊክ ዲዛይንና በሥዕል (illustration) ዝግጅት ሥራ ከአምስት ዓመት በላይ የሥራ ልምድ ሊኖራቸው ይገባል። በቅድመ ሕፃናት እድገት ዘርፍ የመረጃ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና የመገናኛ ሰነዶችን በግራፊክ ዲዛይን፣ በሥዕል ዝግጅትና በሕትመት ሥራ የማዘጋጀት ልምድ ሊኖራቸው ይገባል።
  • ጥራት ያላቸው ህትመቶችን፣ ሥዕሎችን፣ መረጃን በምስል የሚያቀርቡ ሰነዶችንና ለሕትመት እና ለዲጂታል ሚዲያ የተዘጋጁ ሥራዎችን የሚያሳይ የሥራ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  • እንደ Adobe InDesign፣ Adobe Illustrator፣ Adobe Photoshop፣ CorelDRAW ወይም ተመሳሳይ የዲዛይን ሶፍትዌሮችን በብቃት የሚጠቀሙ ባለሙያዎች ሊኖሯቸው ይገባል።
  • በውጤት ላይ በማተኮር፣ በተለያየ ባህልና አመለካከት ካላቸው ሰዎች ጋር በተነሳሽነትና በብቃት መሥራት መቻል አለባቸው።
  • ከተለያዩ የሥራ ክፍል ባለሙያዎችና ቡድኖች ጋር በትብብር፣ በጥሩ ግንኙነትና በሙያዊ ሥነ-ምግባር መሥራት መቻል አለባቸው።
  • በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሥራን ማከናወን፣ የተቀመጡ የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜያትን ማክበርና በተለዋዋጭ የሥራ ሁኔታ ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎችን ማስተናገድ መቻል አለባቸው።
  • የቋንቋ ችሎታ:- በአማርኛና በእንግሊዝኛ ጥሩ የመናገር፣ የመጻፍና የመግባባት ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል። ተጫራች ድርጅቱ ለዚህ ሥራ የሚያቀርባቸውን ባለሙያዎች የትምህርት ደረጃ፣ ሙያዊ ብቃትና ተዛማጅ የሥራ ልምድ የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ማቅረብ አለበት። የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት እድገት ማዕከል (AfC-ECD) ተጫራቾች ያቀረቧቸውን የማጣቀሻ መረጃዎች፣ የሥራ ናሙናዎች፣ ሕጋዊ ብቁነትና ሌሎች መረጃዎች የማረጋገጥ መብት አለው።

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ተጫራቾች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማቅረብ አለባቸው።

4. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ

ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 90 (ዘጠና) ቀናት ነው።

5. የቴክኒክ ሰነድ አቀራረብ

የቴክኒክ ሰነዱን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ቅጂ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

6. የፋይናንስ ሰነድ አቀራረብ

የፋይናንስ ሰነዱን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ቅጂ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

7. የጨረታ ሰነዶች አዘገጃጀትና አቀራረብ

  • ከዋናው የጨረታው መወዳደሪያ ሀሳብ በተጨማሪ የቅጂ ብዛት 1 ያስፈልጋል ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያዩ ኢንቨሎፖች (ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሃሳብ እና ፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሀሳብ) ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው (CPO) በተለየ ፖስታ ታሽጎ ከፋይናንስ ሰነዱ ጋር መቅረብ አለበት።
  • ኦሪጅናልና እና ቅጂ ሰነዶች በግልጽ ምልክት ተለይተው መቅረብ አለባቸው።

መገናኛ ስልክ : ኢፍቱ አሕመድ +251912924820

የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል

✨ messages.ai_summary
The Africa Center for Early Childhood Development (AfC-ECD) seeks a firm to provide graphic design and illustration for its publications, reports, training and awareness materials on a one-year contract. Staff need a degree and 5+ years of design experience; samples required.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender