በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ለተለያዩ ቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ላይ የሚውሉ አዲስና ኦርጅናል የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በተቀመጠው መመሪያና ግዴታዎች መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር:- ተአጥዘ/ግጨ/01/2019
በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ለተለያዩ ቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ላይ የሚውሉ አዲስና ኦርጅናል የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በተቀመጠው መመሪያና ግዴታዎች መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ማንኛውም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች መጫረት ይችላል።
1. የግዥ ፈፃሚ አካል ስም:- በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ
2. የዕቃው ዓይነት የቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪ የመለዋወጫ ዕቃዎች
3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
3.1 አግባብ ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒውን በማቅረብ ዋናውን ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችል።
3.2 የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ኮፒውን በማቅረብ ዋናውን ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችል።
3.3 የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3.4 ከ2 እና ከዚያ በላይ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ የልማት ድርጅቶች የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስጋና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
3.5 የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሠነድ ከተከፈተ በኋላ በቴክኒክ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች የተወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት በክምችት እንዳላቸው ለማየት ለሚመጡ የኮሚቴ አባላት ማሳየት ይኖርባቸዋል። በተለያዩ ምክንያት ሳያሳዩ ቢቀሩ ከውድድር ውጪ ይደረጋሉ።
3.6 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቃሊቲ የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ በሚገኘው መስሪያ ቤት የግዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ።
3.7 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ፡
3.8 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ዕቃ የአጠቃላይ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል (CPO) ሲዘጋጅ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደር ጥገና ዘርፍ ስም መዘጋጀት አለበት።
3.9 ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
3.10 የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ የግዥ ክፍል ይከፈታል። ሆኖም የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀናት እንዲሁም የዕረፍት ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን የሚተላለፍ ይሆናል። እንዲሁም ተጫራች በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ሳይገኝ ቢቀር የጨረታው መከፈት ሂደት አያስተጓጉለውም።
3.11 ተጫራቾች ለተለያዩ ቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ላይ የሚውሉ አዲስና ኦርጅናል የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች የሚጫረቱበትን ዋጋ በግልፅ እንዲሁም በሚታይና ግልፅ በሆነ መንገድ ከስርዝ ድልዝ በፀዳ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ አንድ ዋና (original) እና አንድ ቅጂ (copy) ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግና በመፈረም የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደር ጥገና ዘርፍ አድራሻ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከጠዋት 2:00 6:00 ከሰዓት 7:30 - 11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቃሊቲ በሚገኘው የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል። የጨረታ ሰነዱ ሳጥን ውስጥ ከመግባቱ በፊት መመዝገብ ይኖርበታል።
3.12 የጨረታ ሰነድን ሳይገዛ የተጫረተ ማንኛውም ድርጅት ከተገኘ ከጨረታው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
3.13 ዘርፉ ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ አድራሻ ቃሊቲ ጉምሩክ የባቡር መጨረሻው ጣቢያ ፊት ለፊት ከአዋሽ ባንክ ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ ግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ጊቢ ውስጥ ስልክ ቁጥር 0983310199/0913630237 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
