Tender Detail

Tender Details

  • Company Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address ሞጆ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0222369094
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Sector Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ግልጽ የጨረታ ሽያጭ

Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ-13/2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1425/2018 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የተተውና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት ELECTRIC PIPE WELDING MACHINE, S/S FLOOR DRAIN, S/S SINGLE BOWEL KITCHEN SINK & OTHERS! PVC PLASTIC MOBILE SHELL COVERS FOR SMART PHONE: BRASS CHECK VALVE, BRASS FOOT VALVE, BRASS STRAINER FILTER VALVE & OTHERS! MAPE PLANSEA 2881 ሽቶ አልባሳትና ጫማ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች ከአክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 6:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:00 እስከ ቀኑ 10:30 እና ዓርብ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:30 እስከ ቀኑ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀነ 5:30 መመልከት ይችላሉ::
  2. የጨረታ ሰነዱን ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም /ድረገፅ/ ኦንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ::
  3. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸዉ፤ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ::
  4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በ ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሰርተዉ አክሽን ኢትዮጵያ ሂደዉ በማስያዝ ወይም በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች ኦንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም:: በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፤ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም::
  6. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ::

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Summary
Modjo Customs Branch Office sells abandoned and confiscated goods, including electric pipe welding machines, stainless floor drains and kitchen sinks, phone covers, brass valves, perfume, clothing and shoes, via Auction Ethiopia. Open bid.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender