ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን የተጎዱ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
Berhan Insurance S.C (ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ፤የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች (ፕላስቲክ ነክ የሆኑና ያልሆኑ ፤ባምፐሮች ማስከፈያዎች ፤ኮፈኖች ፤በሮች ፤ፈረፋንጎዎች የተለያዩ መብራቶች ፤ስፖኪዮዎች ፤ ራዲያተር ጎማዎች፤ ኩለር ፤ኮንደንሰር የተለያዩ ገቢናዎች...ወዘተ) እንዲሁም ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ከዋናው መስሪያ ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የተጎዱ ንብረቶች ማከማቻ ቦታ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቃሊቲ 40/60 ኮንደሚኒየም በኩል ገባ ብሎ በተለምዶ የቆላ ዝንብ አካባቢ (ጨፌ ሰፈር) የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት የሚፈልገውን የንብረት ዓይነት እና ያቀረበውን የጨረታ ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ ፤የጨረታ ማስከበሪያ የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 15 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስም በማስያዝ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ በሥራ ቀናት ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03 ቦሌ ወሎ ሰፈር ጋራድ ሲቲ ሴንተር 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ ለሚጫረቱበት የዕቃ አይነት ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ለተሸነፉ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ይመለስላቸዋል። ለጨረታ አሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ተሽከርካሪ ወይም መለዋወጫ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል።
- አሸናፊዎች በጨረታው ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ አክለው በመክፈል የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ እቃዎችን መረከብ ይኖርባቸዋል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያሸነፉትን ንብረት ከፍለው ካልወሰዱ ኩባንያው ለጨረታ ያስያዙትን ሲፒኦ ገቢ አድርጎ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልጽ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር በቀረበው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል።
- ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ወይም ሌላ ክፍያ የሻጩ ኃላፊነት ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ዕቃ ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ።
- ጨረታው ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8:30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011467-44-23/46 ወይም 0114-70-40-54 መደወል ይቻላል።
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Berhan Insurance S.C. sells by tender, as is, damaged heavy and light vehicles taken over after claim payments, vehicle parts (bumpers, bonnets, doors, lights, mirrors, radiators, coolers, cabins and more) and its own used vehicles. Items can be viewed at its Kality storage yard.
