የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ሮቤ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 ቢጋ ወቅት ያመረታቸውን የዳቦ ስንዴ (824.10 ኩንታል) እና የገብስ (453.12 ኩንታል) ዘር ዝርያዎች በጨረታ ቁጥር 01/213/2019 በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ሮቤ
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/213/2019
የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ሮቤ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 ቢጋ ወቅት ያመረታቸውን የተለያዩ የስንዴ እና ገብስ ዘርያ ብዛት የዳቦ ስንዴ ብዛት በኩንታል 824.10 (ስምንት መቶ ሃያ አራት ኩንታል ከ 10 ኪ.ም) እና ገብስ ብዛት በኩንታል 453.12 (አራት መቶ ሀምሳ ሶስት ኩንታል ከ 12ኪ.ም) በማሽን ተበጥረው ንፁህ ለማግባቢና ለፋብሪካ የሚውሉ የዳቦ ስንዴ እና ገብስ ዘር ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ። ስለዚህ በሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ባለቤቶች ፤መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ ግለሰብ ነጋዴዎች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) Oromia Agricultural Research Institute Internal Revenue B ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000466928357 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 10 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ፤ ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የስንዴ ዝርያዎች ዓይነት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20 % (20 ፐርሰንት) የያዘ ሲፒኦ ብቻ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱበትን ሰነድ በመግዛት 1ኛ, ኦሪጂናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ እና 2ኛ, ዋጋ የተሞላበት ኮፒ ሰነድ ለሁለቱንም ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት እለት እና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ላይ የድርጅታቸውን ወይም የግለሰቡን የነጋዴውን ስም እና ሙሉ አድራሻ ስልክ ቁጥር በመፃፍ መፈረም ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሲናና ፡ ግብርና ምርምር ማዕከል ስም ያስያዙትን ሲፒኦ ፡ ኦሪጅናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በእያንዳንዱ የመወዳደሪያ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድ እና ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ስንዴውን መረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0930292332 ደውለው ይጠይቁ ።
የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ሮቤ
✨ messages.ai_summary
Sinana Agricultural Research Center, via the South East Oromia Zone Plan and Finance Office in Robe, sells by open tender 824.10 quintals of bread wheat and 453.12 quintals of barley seed it produced in 2018. Open to food factories, organisations and individual traders.
