የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኝ ቤት በድጋሚ የሐራጅ ሽያጭ
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት የህፃን ዮሴፍ አምዴ (ሞግዚት መቅደስ ደሳለኝ) እና የፍ/ባለዕዳ አስገደች ወርቅነህ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/114858 በ30/07/2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/117741 በ9/10/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ለማስጽፈም ይቻል ዘንድ ፍርድ ያረፈበት ቤት በቀድሞው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ቀበሌ 10/10 በአሁኑ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር 009 የቦታው ስፋት 161 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 7,806,959 (ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል:: ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.119486 በቀን 21/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 1,951,739.75 ( አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ከ75/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 5 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል::
የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮበፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታየሌለበት መሆኑን እንገልፃለን::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
