Tender Detail

Tender Details

  • Company HORIZON ADDIS TYRE (ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-442-15-55
  • Website
  • Deadline05 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 400.00 (የማይመለስ)
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:20 ሰዓት
  • Sector Sales, Disposals And Foreclosure , Other Sales

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

HORIZON ADDIS TYRE (ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማ)


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2019

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. የብረት ሞልዶች
  2. የብረት ኮንቴነሮች
  3. ራድያል ሽቦዎች
  4. ስክራፕ ከምፓውንድ
  5. የብረት፣ የፕላስቲክ እና የእንጨት ፓሌቶች
  6. የተለያየ መጠን ያላቸው ብላደሮች
  7. ያገለገሉ መካኒካል ማሽን ስፔርፓርቶች
  8. አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ፍላፖች
  9. አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የጎማ የውስጥ ላስቲኮች(ከመነዳሪ )
  10. የተጋቡ የብረት በርሜሎች
  11. ያገለገሉ እና አዳዲስ የውጪ ብራንድ ጎማዎች
  12. በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ ያገለገሉ የተለያዩ የማሽን ዘይቶች
  13. ብረታብረቶች
  14. እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች

በመሆኑም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በግልፅ ሞልተው፣ ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ሳሪስ በሚገኘው በዋናው ሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:05 ሰዓት ይታሸጋል። ጨረታው ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
  4. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ:- ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ስልክ ቁጥር 011-442-15-55/234 ወይም 251974024142 መጠየቅ ይቻላል:

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

Summary
Horizon Addis Tyre PLC is selling metal moulds and containers, radial wire, scrap compound, pallets, bladders, used machine spare parts, tyres, inner tubes, used oils, scrap metal and other items by open bid.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender