በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካርዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ግልፅ የጨረታ ቁጥር 01/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካርዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በዚሁ መሠረት:- በግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2019 በ12/03/201 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች
- ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ ወይም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ ያለው/ያላት
- በጨረታ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ገቢ በሚገኘው ተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው::
- የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም ::
- በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ሙድአነኖ ቢሮ በመቅረብ ከ03/03/2019 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል::
- ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም::
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው::
- ተጫራቾች በተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ለመግዛት የሚሰጠዉን ዋጋ ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 3:45 ድረስ በድሬዳዋ ሙድአነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
- ጨረታው ከጠዋቱ 3:50 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ጉምሩክ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል::
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፈለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል::
- ከላይ በተራ ቁጥር 12 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል::
- የጉምሩክ ኮሚሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 ( 0912885746 ) መደወል ይቻላል::
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
Summary
Dire Dawa Branch of the Customs Commission is selling various confiscated vehicles, as is, held at its Dire Dawa vehicle warehouse. Bidders must be Ethiopians over 18 and may inspect the vehicles before bidding. Open bid.
