ዳሽን ባንክ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎች (የቢሮ ዕቃዎች፣ ማሽኖች እና ጀነሬተሮች) የጨረታ ሽያጭ
DASHEN BANK S.C (ዳሽን ባንክ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሽያጭ DB/053/2019
ዳሽን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሎት 1 ለሶስተኛ ዙር እና በሎት 2 ለአንደኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች ቄራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡን ብረቶችን በባንኩ መጋዘኖችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው::
- ከላይ በተራቁጥር 4 የተገለፀውንየጨረታማስከበሪያዋስትናያላስያዘእናበ ሠነዱየተቀመጡሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል::
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከ አዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከዳሽን ባንክ አ.ማ. ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል::
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በ10ኛው ቀን ማለትም ሕዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ06:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ 09:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::
- በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት/ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል:: ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል::
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ውል በፈረሙ በ10 የሥራ ቀናት ዉስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
- ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል::
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-4655552 ወይም 011-4706065 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ሎት 1 (ሶስተኛ ዙር ጨረታ)
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | SWICH | በቁጥር | 26 |
| 2 | METAL DETECTOR | በቁጥር | 60 |
| 3 | Kama Small Generator | በቁጥር | 4 |
| 4 | LOST AND FOUND DISPLAY BOARD | በጥቅል | በጥቅል |
| 5 | NOTICE BOARD | በጥቅል | በጥቅል |
| 6 | WALL CLOCK | በቁጥር | 4 |
| 7 | EPSON TERMAL PRINTER | በቁጥር | 35 |
| 8 | NOTE COUNTING MACHINE FOR TELLER | በቁጥር | 17 |
| 9 | MANAGERIAL TABLE | በጥቅል | በጥቅል |
| 10 | COMPUTER STAND TABLE | በጥቅል | በጥቅል |
| 11 | HIGH BACK SWIVEL CHAIR | በጥቅል | በጥቅል |
| 12 | STORAGE CABINET | በጥቅል | በጥቅል |
| 13 | LOW BACK SWIVEL CHAIR | በጥቅል | በጥቅል |
ሎት 2 (አንደኛ ዙር ጨረታ)
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | Adding machine | በቁጥር | 17 |
| 2 | Cash box | በቁጥር | 7 |
| 3 | Computer stand table | በጥቅል | በጥቅል |
| 4 | Coffee table | በጥቅል | በጥቅል |
| 5 | Counter chair | በጥቅል | በጥቅል |
| 6 | Dixon shelf | በቁጥር | 7 |
| 7 | Fax machine | በቁጥር | 2 |
| 8 | File cabinet | በቁጥር | 5 |
| 9 | Guest chair | በጥቅል | በጥቅል |
| 10 | Guest chair 2 and 3 seater | በጥቅል | በጥቅል |
| 11 | High back chair | በጥቅል | በጥቅል |
| 12 | Lost and found display board | በቁጥር | 2 |
| 13 | Low back chair | በጥቅል | በጥቅል |
| 14 | Managerial table | በጥቅል | በጥቅል |
| 15 | Metal detector | በቁጥር | 4 |
| 16 | Multi-currency detector | በቁጥር | 15 |
| 17 | Note counting for teller | በቁጥር | 117 |
| 18 | Notice board | በቁጥር | 2 |
| 19 | Monitor | በቁጥር | 13 |
| 20 | System unit | በቁጥር | 14 |
| 21 | Kyocera printer | በቁጥር | 6 |
| 22 | Scanner | በቁጥር | 50 |
| 23 | Single pedestal table | በጥቅል | በጥቅል |
| 24 | Sofa | በቁጥር | 10 |
| 25 | Storage cabinet | በቁጥር | 3 |
| 26 | Wall clock | በቁጥር | 2 |
| 27 | Safe | በቁጥር | 14 |
| 28 | Fire resistant | በቁጥር | 2 |
| 29 | Kama big generator | በቁጥር | 1 |
| 30 | ATM | በቁጥር | 14 |
ዳሽን ባንክ አ.ማ.
አዲስ አበባ
ዳሽን ባንክ አ.ማ.
✨ messages.ai_summary
Dashen Bank is selling used fixed assets as-is in 2 lots, including office furniture, chairs and tables, metal detectors, note counting machines, printers, monitors, safes, generators and ATMs. Items can be viewed at the bank stores. Open bid.
