የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የCHERY እና Karry የንግድ ተሽከርካሪዎች የሐራጅ ሽያጭ
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ ፍቅሩ ታጋሽ እና በፍ/ባለዕዳ ኢል አውቶ ኢንጅነሪንግ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.05400 በቀን 12/07/2017ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.05400 በቀን 24/4/2017 ዓ.ም የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.10224 በቀን 11/09/2017ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.10224 በቀን 4/10/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1ኛ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ ኮድ 3-B79610 ኢ.አ CHERY ARR120-5 ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ.ህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ በ4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: 2ኛ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ 3-B67520 ኢ.አ Karry K-60 የንግድ ተሽከርካሪ ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ 2,100,000 ( ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ.ህ)ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ በ4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: 3ኛ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ ኮድ 3-B64455 ኢ.አ Karry K-60 የንግድ ተሽከርካሪ ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ 2,100,000 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ.ህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ በህዳር 24 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ በ5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: 4ኛ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦትየመኪና ማቆሚያ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ 3-B79483 ኢ.አ CHERY ARR120-5 የንግድ ተሽከርካሪ ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ 1,500,000 (አንድ ሚሊዮኝ አምስት መቶ ሺ.ህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ በህዳር 24 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P. O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤ/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አካውንት ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት:: በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
