Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline09 Dec 2026, 2:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4ኛ (ብር 1,270,781.25) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening dateህዳር 30 ቀን 2019 ዓ/ም (ምዝገባ እንደተጠናቀቀ)
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኙ ቤቶች የሐራጅ ሽያጭ (በድጋሚ)

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሪት ሄርሚላ ቴዎድሮስ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ሜሮን ለገሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/109243 በ30/7/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/111438 22/08/2016ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ለማስፈፀም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 274 በካ/ቁ/ወ13/027101/30/661/00 በሰናይት ወርቅነህ እና ሄርሚላ ቴዎድሮስ ስም በተመዘገበ ይዞታ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ ሁለት ከፍል ቤት ከንግድ ቤቱ፤ሁለት ከፍል ዕቃ ቤቶች በብሎኬት የተሰሩ ሁለት ከፍል ቤቶች በብሎኬት የተሰሩ ሽንት ቤትና ሻውር ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ አንድ ከፍል ቤት አጠቃላይ የቤቶቹ ስፋት 104.56 ካ/ሜ የሆነ አጠቃላይ የንፅፅር ድርሻ 121.83 ካ/ሜ በይዞታው ውስጥ የፍርድ ውሳኔ ያላረፈባቸው ቤቱ ያሉ መሆኑ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,083,125 (አምስት ሚሊዮን ሰማኒያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሀያ አምስት ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል:: ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.111438 በቀን ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 1,270,781.25 ( አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ አንድ ከ25/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል::የተጫራቾች ምዝገባ 8:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት:: በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Federal Courts Judgment Execution Office is re-auctioning several blockwork rooms and storerooms (104.56 square metres) within a compound in Addis Ketema sub-city, Woreda 13, Addis Ababa, under a court order. Bidders deposit a quarter of the starting price by CPO.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender