የወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ያገለገሉ መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የውሃ ቱቦዎች እና ቁርጥራጭ ብረቶች ሽያጭ (በድጋሚ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ወረዳው በተለያዩ ጊዜ በግዥ፤በዕርዳታና በስጦታ ያገኟቸው ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም ያገለገለ መኪና፤ የውሃ ቱቦ ባለብረት የተለያዩ እንች፤ የሞተር ሳይክሎች፤ቁራሌ ብረቶች እና ሌሎች ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:-
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ዝርዝር ጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት /ክፍል/ በመውሰድ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ አንድ ኦሪጂናልና አንድ የኦሪጂናል ኮፒ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከገዙ በኃላ ከጨረታው ቀን በፊት ንብረቶቹን በአካል ለማየት ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፉትን ዋጋ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ መደበኛ አካውንት ሙሉ በሙሉ ገብ ስያደረግ ያሸነፈውን ንብረት ወዲያኑ ይረከባል:: ሌሎች ዝርዝር ሂደቶች በጨረታ ሰነዱ የሚካተቱ ይሆናል::
- የመኪና እና ሞተር ተሽከርካሪዎች ስም ዝውውር በገዥ ይሸፈናል፤ የተሽከርካሪዎች ታርክ ማስረጃ መ/ቤቱ ለገዥው ያቀርባል:: ሌሎች ንብረቶች የይለፊ ደብዳቤ ይሰጣል::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ 16ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 5:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/ ይከፈታል:: መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-16-59-96-57/ 09-16-35-11-13/-09-25-14-75-81 ይደውሉ፤
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kindo Koysha Woreda Finance and Plan Office (Wolaita Zone, South Ethiopia) is re-tendering the sale of used items including a vehicle, motorcycles, steel water pipes and scrap metal. Items can be viewed after buying the bid document. Open bid.
