Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address በቦሌ ሚካኤል መንገድ በካርጎ ቅጥር ግቢ ውስጥ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116651351
  • Website
  • Deadline12 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityበግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO)፤ በሐራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/መቶ ሺህ/
  • opening dateበዛው ቀን በ8:15 የሚከፈት ይሆናል።
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ እና በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 37/2019 38/2019፣ 39/2019፣ 40/2019፣ 41/2019፣ 42/2019፣ 43/2019 እና 44/2019 የጨረታ ማስታወቂያ፤

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ እና በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 37/2019 38/2019፣ 39/2019፣ 40/2019፣ 41/2019፣ 42/2019፣ 43/2019 እና 44/2019 የጨረታ ማስታወቂያ፤

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸም ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱየተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦክስ እና ልዩልዩ ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታቁጥር 37/2019 በቀን 03/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 38/2019 በቀን 7/3/2019 ዓ.ም፣ጨረታ ቁጥር 39/2019 በቀን 10/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 40/2019 በቀን 14/3/2019 ዓ.ም ፣ጨረታ ቁጥር 41/2019 በቀን 17/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 42/2019 በቀን 21/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 43/2019 በቀን 24/3/2019 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 44/2019 በቀን 28/3/2019 ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን።

በመሆኑም፤

  1. በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00-11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00-6:00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ ህዳር 03/2019 ዓ/ም፣ ህዳር 07/2019 ዓ/ም፣ ህዳር 10/2019 ዓ/ም፣ ህዳር 14/2019 ዓ/ም፣ ህዳር 17/2019 ዓ/ም፣ ህዳር 21/2019 ዓ/ም፣ ህዳር 24/2019 ዓ/ም፣ ህዳር 28/2019 ዓ/ም ከቀኑ በ8:00 ተዘግቶ በዛው ቀን በ8:15 የሚከፈት ይሆናል።
  5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረበው ቅጽ መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ ፣የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግኘ ዋጋ መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታ ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው።
  9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል። በተራ ቁጥር 01 - 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 37/2019 በቀን 3/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 38/2019 በቀን 7/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 39/2019 በቀን 10/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 40/2019 በቀን 14/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 41/2019 በቀን 17/3/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 42/2019 በቀን 21/3/2019 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 43/2019 በቀን 24/3/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሂድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል።
  10. በሐራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/መቶ ሺህ/ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION.
  11. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃለን።
  12. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በቅ/ጽ/ቤቱ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አፈፃፀም ለማስፋት፣ፈጣንየዕቃዎች ማስወገድ ሥራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ በመሰብሰብ እንዲቻልጨረታዎችን በወረቀት አልባ (online) አሠራር ለማስኬድ ለአክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ ጋር ለመስራት በመታሰቡ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በአክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ በወረቀት አልባ (online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።
  15. አክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251905115511 ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116684537 እና 0116684193 ደውሎ ይጠይቁ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Customs Commission Addis Ababa Airport Branch sells confiscated goods as is, by open tender and auction in eight rounds: electronics, mobiles, vehicle parts and accessories, clothing, shoes, gearboxes and more. Bidders need a sector trade licence, TIN, VAT and tax clearance.
Save Tender