የቦንጋ እጸዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፤ የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦታ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል።
የቦንጋ እጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019
የቦንጋ እጸዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፤ የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦታ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል።
- ሎት 01 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ
- ሎት 02 ለቢሮ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 03 መኪና ጎማ ግዥ(የሎንግ ቤዝና የፎርድ መኪና)
- ሎት 04 የመኪና ማቆሚያ ሼድ ግንባታ
- ሎት 05 የዘር ጥራት ፍተሻ (GOT) ጣቢያ አጥር ግንባታ
በዚሁ መሠረት
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- ህጋዊ የኮንስትራክሽን የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የዘመኑን ግብር የከፈለበትና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (Tin no) ያላቸው፤
- በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 01 እና 02 ብር 4000፤ ለሎት 03 ብር 5000፤ ለሎት 04 እና 05 ብር 10000 በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 01፤02 እና ለሎት 03 ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም ለሎት 04 እና 05፤ 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር ብቻ በማዕከሉ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000099955361 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ ከማዕከሉ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላል።
- ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የግዥን እንዲሁም ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የዘር ጥራት ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ እና የመኪና ጥገና የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን ዋናና ኮፒ ለየብቻ ተፈላጊ መረጃዎች ጋር በፖስታ በማሸግ በቦንጋ እፅ/ዘር/ጥ/ቁ/ማዕከል የግዥና ፋይ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦታ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ ተጫራቾች ቴክኒካና ፋይናንሻል ሰነድ ሲመልሱ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ ላይ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።
- ጨረታው ለግዥዎች በ16ኛው ቀን የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ በ22ኛው ቀን ከሰዓት 8፡30 ታሽጎ በዕለቱ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። የተጠቀሰው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- በጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ማንኛው ተጫራች ማብራሪያ መጠየቅ የሚችለው ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ(10) ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል።
- ውጤት አስመልክቶ ቅሬታ ማቅረብ የሚችለው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለሰባት (07) ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው
- የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦታ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ አሸናፊው ሲረጋገጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት ውል ማስከበሪያ (performance bond) ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርቦ ውል በመግባት የሚያቀርባቸውን ዕቃዎች እስከ ማዕከሉ ግቢ ድረስ ማቅረብ አለበት። ይህ ሳይሆን በውሉ መሠረት ዕቃዎች ባይቀርቡ ስራው ቢስተጓጎል በግዥ ኤጀንሲ ደንብ ወይንም በኮንስትራክሽን ህግ መሠረት ውል ተቀባይ እንዲጠየቅ ይደረጋል።
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጸ ነገር ግን በእያንዳንዱ ሎት ላይ የሚከተሉ ሀሳቦች በጋዜጣ እንደወጣ ይቆጠራል።
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0936725132/0910215680 ደውለው ማረጋገጥ ይቻላል።
የቦንጋ እጸዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል
✨ messages.ai_summary
The Bonga Plant Seed Quality Control and Testing Center seeks bidders for office supplies, staff uniforms, vehicle tires, a parking shed, and a seed quality testing station fence. Bidders need a renewed business license, construction license, tax and VAT registration, TIN, and supplier registration.
