ድርጅቱ በዋናው መ/ቤት ስር የሰራተኞች እና የስልጣኞች ክበብ/ካፍቴሪያ ያለው ሲሆን ፍላጎቱ ላላቸው ተጫራጮች በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት መስጠት ይፈልጋል::
ሰላም የሕፃናት መንደር
የጨረታ ማስታወቂያ
ሰላም የሕጻናት መንደር ላለፉት 40 ዓመታት ወላጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት ላጡ ህፃናት የመጠለያ፣ የምግብ፣ የጤና፣ የትምህርትና የማኅበራዊ ስነ ልቦና (ሳይኮሶሻል) አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ተቋም ነው:: ድርጅቱ በዋናው መ/ቤት ስር የሰራተኞች እና የስልጣኞች ክበብ/ካፍቴሪያ ያለው ሲሆን ፍላጎቱ ላላቸው ተጫራጮች በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት መስጠት ይፈልጋል::
በመሆኑም በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ድርጅቶች ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ህጋዊ ማስረጃዎቻችሁን (የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ/ቲን ሰርተፍኬት) በማሟላት በጨረታው ለመሳተፍ እንደምትችሉ እየገለጽን፣ የካፍቴሪያውን ሁኔታ በተመለከተ ከሰኞ - አርብ በስራ ሰአት በተቋማችን በግንባር በመገኘት መመልከት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እየገለጽን ከዚህ በታች በተገለፀዉ መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው በተገለጹት ቀናት ውስጥ የመጫረቻ ሰነዱን ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::
- የጨረታ ሰነዱን ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የፋይናንስና የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ማግኘት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ በሰላም የሕጻናት መንደር ስም የተዘጋጀ 50,000.00 ብር ሲፒኦ በማያያዝ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፣
- እያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ የቴክኒኩን እና የፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቀረብ አለበት::
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያዉ መሠረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተዉ ማስገባት ይኖርባቸዋል
- ጨረታው ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ፣ ከቀኑ በ 8:30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል::
- ተቋሙ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊው ተጫራች በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ውል ተዋውሎ እና ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ለተቋሙ ገቢ ሆኖ ስራውን መጀመር ይችላል::
አድራሻችን፡- ኮተቤ ዜሮ ሁለት አካባቢ ከምትገኘው የሃና ማርያም ቤ/ክ አለፍ ብሎ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት መሆኑን እንገልጻለን::
ስልክ ቁ. 0116462942፣0930011875
✨ messages.ai_summary
Selah Children's Village seeks bidders to take over its on-site staff and trainee cafeteria under contract. Eligible firms need a renewed business license and TIN certificate; the cafeteria can be inspected on-site Monday–Friday during working hours.
