የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of Secure Office Space) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) (የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ ECMA/NCB/OB/02/2019
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of Secure Office Space) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፦
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን የንግድ ባንክ አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የግብር ክሊራንስ፣የግብር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በሪፖርተር ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ጠዋት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጠዋት በ4: 30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ከፍላሚንጎ ሬስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ምናዩ ህንፃ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ 011-5-57-83-27
ኢሜል: Procurement@ecma.gov.et
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Capital Market Authority seeks to procure rental of secure office space via national open tender. Bidders must submit financial and technical documents separately, with renewed business license, registration, VAT and tax clearance, TIN, and a signed anti-fraud declaration.
