በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም ሎት 1- የአልትራ ሳውንድ ባለሙያ ሎት-2-የካፍቴሪያ አገልግሎት ጨረታ ሲሆን ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም ሎት 1- የአልትራ ሳውንድ ባለሙያ ሎት-2-የካፍቴሪያ አገልግሎት ጨረታ ሲሆን ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
* ለካፍቴሪያ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አገልግሎቱን ለማቅረብ የሚያስችሉ መሰረታዊ ዕቃዎችን/ማቀዝቀዣ፣ የሻይ ማሽን፣ ወንበሮችና ጠረጴዛ፣ ቴሌቪዥን፣ ማብሰያ ዕቃዎች፣ ወዘተ...../ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ወይም 3% ተጠቃሚዎች እና ከገቢዎች በልዩ ሁኔታ ለሠራተኞች ለምሳ ድጋፍ ማቅረብ እንዲችሉ ደብዳቤ ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጨማሪ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡
- የውሃ እና የመብራት ፋጀታ በመሥሪያ ቤቱ የሚሸፈን መሆኑንን አውቃችሁ ለሠራተኛው የምታቀርቡትን የምግብ፣ የለስላሳና የሻይ ቡና ዋጋ ላይ በአነስተኛ ዋጋ እና በጥራት እንደምታሩ ማወቅ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ መ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ አድርገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩት በአነስተኛ ዋጋ ድምር ስለሆነ እያንዳንዱን የምግብና የለስላሳ፣ የሻይ ቡና ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ የሁሉም ጠቅላላ ዋጋ ድምር አነስተኛ የሆነ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
- እያንዳንዱ ዝርዝር ላይ ዋጋ አለመሙላት ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
- ለአልትራሳውንድ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በራዲዮሎጂ ቴክኖሎጅ የተመረቀ/ች ዲግሪ ያለው፡፡
- በሙያው ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ የአልትራሳውንድ ሥራ ልምድ ያለው/ያላት፡፡
- የታደሰ የሙያ ፍቃድ ያለውና እና በዘርፉ የተሰማሩበትን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin/ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ባለሙያው የሠራቸውን ውጤት ሲስተም ላይ ማስገባት ግዴታ አለበት፡፡
- ጠቅላላ የአገልግሎቱ ዋጋ ከ10000/አስር ሺ ብር በላይ ከሆነ ዊዝሆልዲንግ ታክስ የሚቆረጥ ይሆናል፡፡
- በሳምንት ለሶስት/3/ ሙሉ የሥራ ሰዓት ወይም ሰኞ ፣ ማክሰኞ እና አርብ መሥራት የሚችሉ እና በሳምንት አምስት /5/ ቀን ማለትም ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስ እና አርብ መሥራት የሚችሉ ሰዓቱን ለይተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የአገልግሎት ክፍያው ከተሰበሰበው ገቢ ላይ ለተቋሙ 50 ፐርሰንት እና ለባለሙያው 50 ፐርሰንት መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ መስፈርቱን አሟልቶ ተወዳድረው ለመጡ ተወዳዳሪዎች መ/ቤቱ ፈተና አውጥቶ አወዳድሮ አሸናፊውን ይለያል፡፡
ለሁለቱም ጨረታ የሚያገለግሉ መስፈርቶች
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሎት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ይህ ጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን 10:00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋውም በ10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ይሆናል፡፡ ጨረታዉ በግልጽ የሚከፈተው በ11ኛው (በአስራ አንደኛው) ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት አገልግሎቶች/ሎት-1-5000/አምስት ሺህ ብር ብቻ/ሎት-2-13000/አስራ ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል ሲፒኦ ስታስይዙ በሎት ከፋፍላችሁ ከሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111546900/011 54 60 29/ 0111 26 80 48 / 47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ :- ጉለሌ ክ/ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ሕንጻ ፊት ለፊት
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Addisu Gebeya Health Center seeks bidders for two service lots: Lot 1 ultrasound specialist services and Lot 2 cafeteria services. Cafeteria bidders need a valid business license, TIN, basic equipment (refrigerator, tea machine, furniture, TV, cooking utensils), and VAT registration or 3% withholding eligibility. Ultrasound bidders need a radiology technology degree, 2+ years' experience, renewed professional license, and TIN.
