Tender Detail

Tender Details

  • Company ተስፋ ድርጅት
  • Address አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113482537
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 12:00 PM
  • magazineThe Reporter
  • Bid Document Priceብር 200
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateጥቅምት 20 ቀን 2019 ከቀኑ 8:00 ሰዓት
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Food Items And Drinks

በድጋሚ የወጣ የተማሪዎች ቁርስና ምሳ ምግብ አቅርቦት (አርሲ ነገሌ እና ወንሾ ወረዳ ት/ቤቶች) - ተስፋ ድርጅት (Hope Enterprises)

ተስፋ ድርጅት


በድጋሚ የወጣ የምግብ አቅርቦት የጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ደቡብ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ስልጠና እና በአስቸኳይ እርዳታ ዙሪያ የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ለሚረዳቸው ተማሪዎች፣

  1. በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ ወረዳ ሮጌ ቀበሌ በሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 600 ለሚጠጉ ተማሪዎች
  2. በሲዳማ ክልል በወንሾ ወረዳ ሲንታሮ ቀበሌ ት/ቤት ለሚማሩ 615 ለሚጠጉ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ቅጽ/ሰነድ ከተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 200 በመግዛት እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ፣ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ በማህተም በተረጋገጠ እና በታሸገ ፖስታ ማስገባት እንደምትችሉ እናስታውቃለን፡፡

በህጋዊ ማህተም ያልታሸገ ፖስታ ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል፡፡

ጨረታው ጥቅምት 20 ቀን 2019 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ:-ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በተጨማሪም አሸናፊ ተጫራቾች ለአንድ የትምህርት ዓመት 2019 ዓ.ም. ባቀረቡት ዋጋ ምግቡን የማቅረብ ሀላፊነት አለባቸው፡፡

ከአማካይ ምግብ ዋጋ በጣም ዝቅተኛ ወይም በጣም ከፍተኛ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ሊያሰርዙ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ: አ.አ ዋናው መስሪያ ቤ/ት አየር ጤና ፣ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0113482537 የመ.ሳ.ቁ 30153 አዲስ አበባ ወይም

ተስፋ ድርጅት (HOPE Enterprises)

✨ messages.ai_summary
Hope Enterprises seeks bidders to supply breakfast and lunch to about 600 students at a school in Roge kebele, Arsi Negele woreda (Oromia), and about 615 students at a school in Sintaro kebele, Wensho woreda (Sidama). Bidders must provide a valid renewed business license and TIN certificate.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender