የማለዳ የለውዝ ቅቤ ምርት አከፋፋዮች ምልመላ - ሕሊና ገንቢ ምግቦች ኃ/የተ/የግ/ማህበር (Hilina Enriched Foods plc)
Hilina Enriched Foods plc ሕሊና ገንቢ ምግቦች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
ለምርት አከፋፋዮች የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ህሊና ገንቢ ምግቦች ኃ/የተ/የግል ማህበር ላለፉት 28 ዓመታት በከፍተኛ ጥራት የነፍስ አድን ምርት ማለትም ፕላምፒነት እያመረተ ለእርዳታ ድርጅቶች ሲያቀርብ ቆይቷል እያቀረበም ይገኛል፡፡ አሁን ደግሞ ለሰፊው ገበያ የሚውል በከፍተኛ ጥራትና ደህንነት የሚመረት ማለዳ የሚባል የለውዝ ቅቤ ይዞ መጥቷል፡፡ ይህን ምርት የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የሚያሟላ እና በከፍተኛ ጥንቃቄ የተመረተ ጣፋጭ ለጤና ተስማሚ የለውዝ ቅቤ ነው፡፡ ይህንን ምርት በአዲስ አበባ፣ በሸገር ከተሞችና በክፍለ ሃገር ማከፋፈል የምትፈልጉ ብቁ አከፋፋዮች ከዚህ በመቀጠል ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ማለትም:-
- ህጋዊ የታደሰ የምግብ አከፋፋይ ፍቃድ ያለው፣
- ምግብና መጠጥ ማከፋፈል ላይ በቂ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- በቂና ደህንነቱን የጠበቀ መጋዘን ያለው፣
- በቂ የሽያጭ ሠራተኛ እና ማከፋፈያ ትራንስፖርት ያለውና
- ጥራቱንና ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ማከፋፈል የሚችል
በድርጅታችን በለገጣፎ በመገኘት የድርጅታችሁን ዝርዝር መረጃ (Company Profile) እና ልምድ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሁም የታደሰ የምግብ አከፋፋይነት ፈቃድ እና Tim Number ኮፒ አድርጋችሁ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 ቀን ውስጥ በአካል እንድታስገቡ ወይንም:-
በEmail BABIY@hilinaFoodseth.com ወይንም BGEZACHEW@hilinafoodseth.com እንድትልኩ ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በ0944036594 ወይም 0975489879 ይደውሉ፡፡
Hilina Enriched Foods plc
ሕሊና ገንቢ ምግቦች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
✨ messages.ai_summary
Hilina Enriched Foods plc seeks eligible distributors for its new "Malada" peanut butter, a high-quality product meeting Ethiopian standards. Scope covers distribution in Addis Ababa, regional cities, and nationwide. Requirements: valid renewed food distributor license, proven food distribution experience, adequate secure warehouse, sufficient sales staff and transport.
Not stated in the notice: opening date, bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
