Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የግዢ፣ ንብረትና ህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 01114378666
  • Website
  • Deadline10 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1 እና 2 ብር 100,000፤ ሎት 3 ብር 300,000 (CPO)
  • opening dateበ11ኛው የስራ ቀን 4:30 ሰዓት
  • Categories Electrical And Electromechanical , Catering And Cafeteria Services

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ለነ/ሴ/ተ/ክ/ማ/ማ (01/001-03/2019)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት ቁጥር የሚገዛው እቃ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን
ሎት 1 የሰልጣኞች ምግብ ለማቅረብ በምናቀርበው የምግብና መስተንግዶ ዝርዝር በቀን ሦስት ጊዜ ማቅረብ 100,000.00 cpo
ሎት 2 ለሠራተኞች ካፊቴሪያ ለማቅረብ በምናቀርበው የምግብና መስተንግዶ ዝርዝር መሰረት ማቅረብ 100,000.00 cpo
ሎት 3 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር 300,000.00 cpo

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና ፋይናንስ መመሪያዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ከተደራጁበት ክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ በመስሪያ ቤቱ የፅህፈት ቤት ኃላፊ ስም የተፈረመ - ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ እና አምራች መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 1000640967181 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ከማዕከሉ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ በማድረግ ቫትን ጨምረው ሞልተው በታሸገው ኤንቨሎፕ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በአራት ፖስታ በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  10. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ነው፡፡

ማሳሰቢያ፤ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪልና ያላቸው አካላት በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

አድራሻ - አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የግዥ ንብረትና ህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ስልክ ቁጥር:-01114378666

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration's Nega Women's Rehabilitation and Skills Development Center seeks bidders for three lots: daily meals for trainees (three times a day), cafeteria food service for staff, and an electric vehicle charger. Bidders must hold a valid business license, tax clearance, supplier certificate, TIN, and VAT registration.
Save Tender