የመፀዳጃ ቤት ፈሳሽ ማስወገጃ መኪና ኪራይ፣ የኮምፒውተርና ፎቶ ኮፒ ጥገና፣ የክበብ አገልግሎት፣ የእስረኛ ቀለብ እና የትርጉም አገልግሎት ግዥ - በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2019 ዓ/ም በጀት አመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች ላይ ከታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሆነ አገልግሎቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም ፡
- የመፀዳጃ ቤት ፈሳሽ ማስወገድ የመኪና ኪራይ
- ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒማሽን የጥገና ባለሞያ
- የክበብ አገለግሎት
- የእስረኛ ቀለብ
- የትርጉም አገለግሎት ግዥ
- ጎሚስታ የሚጫራቱበትን የዕቃ ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 በተከታታይ በስራ ቀን በጉ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፋይናንስ ግዥ አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፤
- የሚጫራቱበትን የዕቃ ዋጋ የሚገልጽ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜውስጥ ለዚው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስገብቶ ይታሸጋል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑ ግብር ለመከፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት የቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወርቀት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀረቡት ዋጋ በየአንደንዱ ሎት ማለትም ተራ ቁጥር 1 እስከ 6 ድረስ ያሉትን ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00/ ሶስት ሺህ ብር / በባንክ የተረጋገጠ በCPO ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካመረ ስራ አፈፃፀም ዋስትና በC.P.O ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በተጠናቀቀበት 10ኛው የስራ ቀን በመ/ቤቱ የስብሰባ አደራሽ በዛው ዕለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ተጨራቻቸው ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል ። ቀኑ በስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጠለው በስራ ቀን 3፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አመራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ ወይም መጠቀም አይቻልም።
- መስሪያ ቤቱ በግዥ ወቅት 20% መጨመር መቀነስ ይቻላል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ለመረዳት
በስልክ ቁጥሮች፡- 0111-56-64-07 /0111-57-91-50/ 09 20-29-88-66/ 09 32-45-10-64
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Gulele Sub-City Police Department seeks eligible suppliers for toilet liquid waste removal vehicle rental, computer/printer/photocopy machine repair, catering, prisoner handcuffs, and translation services. Bidders must provide tax payment proof and registration certificate as goods suppliers.
