የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በሎት1 ሎደር እና በሎት 2 ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ደ/ም/መ/ባ/06/2019
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በሎት1 ሎደር እና በሎት 2 ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
| ሎት | የማሽን/ ተሽከርካሪ/ ዓይነት | የማሽን/ ተሽከርካሪ/ ፈረስ ጉልበት | የማሽን/ ተሽከርካሪ/ የመጫን አቅም በሜ.ኩ | የሥሪት ዘመን እ.ኤ.አ | የሚጠቀመው የነዳጅ ዓይነት | ለአንድ ማሽን/ ተሽከርካሪ/ የሚፈለገው ሰዓት/ወር | ቦንጋ | ታርጫ | ሚዛን |
| 1 | ሎደር | 150 እና በላይ | 3 | 2018 እና በላይ | ናፍጣ | 1000 ሰዓት | 1 | 1 | 1 |
| 2 | ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና | 336 እና በላይ | 14 | 2020 እና በላይ | ናፍጣ | 7 ወር | 8 | 8 | 8 |
በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፡ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያዩ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ «ኦርጅናል» እና «ኮፒ» በማለት እና የጨረታ ማስከበርያዉንም ለእያንዳንዱ ሎት በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዚ ቲም ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ።
- የጨረታዉ አሸናፊ የሚወስነዉ በጨረታ ሰነዱ ዉስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛዉም አቅራቢ ክፍት ነዉ።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታዉ ከቀኑ 11፡30 ድረስ ይሆናል። ጨረታዉ ሎት 1 በ16ኛ ቀን ከጧቱ 3፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ጧት 3፡30 ሎት 2 ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለሎት 2 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በቅድሚያ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታዉ ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸዉን ማቅረብ አለባቸዉ ከጨረታ ደንብና መመሪያ ዉጭ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
- ተጫራቾች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግስት መ/ቤት ቢያንስ አንድ የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
* ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ
በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዚ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 0474527941 /0474527727 ደውለዉ ማነጋገር ይቻላል።
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
✨ messages.ai_summary
South West Ethiopia Peoples' Region Roads Authority seeks to rent, via open tender, Lot 1 loaders and Lot 2 Sinotruk tipper trucks for road construction and maintenance work. Bidders need a valid business/service license, supplier certificate, VAT and TIN registration, and a supporting letter from the domestic revenue office.
