የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአዳማ-አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፣ለአዲስ አበባ እና ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በክፍት ጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ መከራየት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር EEC/NCB/OP/02/2026
የተለያዩ ማሽነሪ መሳሪያ መከራየት በክፍት የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአዳማ-አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፣ለአዲስ አበባ እና ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በክፍት ጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ መከራየት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የግዥ አፈፃፀም ሕጎች እና የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ በተገለጸው የክፍት ጨረታ ሥነ ሥርዓት መመሪያ መሠረት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.0o( አስራ አምስት ሺህ ብር) (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ (Unconditional Bank Guarantee) የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ማስራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ 300 ( ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የዕቃው ዝርዝር እና አገልግሎቶቹ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች (specification)ተያይዟል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ የጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቢያንስ ሶስት ወር የሚጸና መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ ማዘጋጀትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጥዋቱ በ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡
- ጨረታው የቴክኒክ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል፡፡
- መ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ኢ.ኢ.ኮ) ሕንጻ 1 ሁለተኛ ፎቅ፡ የግዥ ንብረትና ፋሲሊቲአስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቡድን ቢሮ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ስልክ ቁጥር +251-924-053-307/+251-11- 897-469/+251-922-346-904
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Engineering Corporation seeks suppliers to rent out construction machinery for road projects in Adama-Assela, Chefe Donsa, Addis Ababa and Harar. Bidders must hold a valid business license, VAT registration, and tax compliance proof. Lowest-priced technically compliant bid wins.
